1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአየር ጠባይ ፍትህ አሁኑኑ!

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 10 2002

በኢትዮጵያ አርባ የሚሆኑ የሲቪል ማኅበራት ጥምረት የአየር ጠባይ ፍትህ አሁኑኑ የሚል መፈክር ያዘለ ፊርማ በማሰባሰብ ላይ ነዉ።

https://p.dw.com/p/KBPl
በማልዲቭ የዓሳ አጥማጆች ባለኢንዱስትሪ አገራት CO2 እንዲቀንሱ በፊርማ ሲጠይቁምስል AP

የፊርማዉ ዋና ዓላማ በኮፐንሃገን ዴንማርክ የፊታችን ህዳር ወር ማለቂያ የሚጀመረዉ ዓለም ዓቀፍ የአየር ጠባይ ለዉጥ ጉባኤ ለአዳጊ አገራት ብሎም ለሁሉም የሚበጅ ስምምነት ላይ እንዲደርስ ግፊት ማድረግ ነዉ። በዚህ ጉባኤ ከሚሳተፉ አገራት መካከል ኢትዮጵያ አፍሪቃን የመወከል ድርሻም ይዛለች። ወደዚያ የሚያቀናዉ የልዑካን ቡድን ደግሞ በአየር ጠባይ ለዉጥ መዘዝ የተጎዱ ወገኖቻችን የገጠማቸዉን ችግር በተጨባጭ ተረድቶ በጉባኤ እንዲያቀርብ ይጠበቃል። ዝርዝሩን ከሙሉ ጥንቅሩ ይከታተሉ።

ሸዋዬ ለገሠ/አርያም ተክሌ