1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአይነስዉራን የኮንፒዉተር ማሰልጠኛ ተቋም

ሰኞ፣ ኅዳር 15 2001

በአገራችን ማየት የተሳናቸዉ ወጣቶች ማየት ከሚችሉት በዉቀት እና በሃሳብ ሳያንሱ በነገሮች አለሟሟላት ብቻ በስራቸዉ ወደፊት መግፋት ሲሳናቸዉ እና ሲቸገሩ እናያለን። አንዳንድ እድለኛ አይነስዉራን ተማሪዎች ደግሞ በትምህርት ቤት በመልካም ፈቃደኛ አንባቢን በማግኘት ጥርሳቸዉን ነክሰዉ ትምህርታቸዉን የሚያጠናቅቁም ጥቂቶች አይደሉም።

https://p.dw.com/p/G1Dd
ፈረንሳዊዉ ሉይስ ብሪል በ 3 አመቱ በደረሰበት ድንገተኛ አደጋ የአይን ብርሃኑን አጥቶአል። በ 16 አመቱ በአለማችን አይነ ስዉራን የሚገለግሉበትን ብሪል ፈለሰፈ።
እ.አ አቆጣተር 1994 አ.ም በአገራችን በወጣዉ ማየት የተሳናቸዉ ሰዎች ቁጥር መዘርዝር እንደሚያሳየዉ ከአንድ ነጥብ ተኩል ሚሊዮን በላይ ማየት የተሳናቸዉ ወገኖች ይገኛሉ። የሚያሳዝነዉ አብዛኛዎቹ ማየት የተሳናቸዉ ግለሰቦች የአይን ብርሃናቸዉን ያጡት በቀላሉ በህክምና ፈዉስ በሚያገኙ እንደትራኮማ ግላኮማ አይነት፣ የአይን በሽታዎች ሲሆን ሌላዉ በግጭቶች እንዲሁም ተፈጥሮዋዊ ሁኔታዎች ነዉ። በአገራችን ብቸኛዉና የመጀመርያዉ የአይነስዉራን የኮንፒዉተር ማሰልጠኛ ድርጅት ከተቋቋመ ስምንት አመት ሲሆነዉ የአለማየት ትርጉምን ያሳጣ መሆኑም ይነገርለታል። በርካታ ወጣቶችንም በመርዳት ላይ ይገኛል። ስለዚህ የኮንፒዉተር ማሰልጠኛ ድርጅት የምንለዉ ይኖረናል አብራችሁን ያድምጡ