1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአይ ኤም ኤፍ የኤኮኖሚ እድገት ጠቋሚ ዘገባ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 18 2008

ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው የአፍሪቃ ሃገራት መካከል ኮትዲቯር፣ኢትዮጵያና ታንዛንያ የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ያስመዘግባሉ ብሏል አይ ኤም ኤፍ።እንደ ድርጅቱ በአማካኝ የ7% እድገት ይኖራቸዋል።

https://p.dw.com/p/1GwVG
Washington IWF Logo Symbolbild
ምስል Getty Images/AFP/M. Ngan

[No title]


አለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት(አይ ኤም ኤፍ) በጎርጎሮሳዊው የ2015/2016 ከሰሀራ በስተደቡብ የሚገኙ የአፍሪቃ ሃገራት የኢኮኖሚ እድገት ጠቋሚ ዘገባ አውጥቷል። በሪፖርቱ መሰረት ሀገራቱ ከሞላ ጎደል ያስመዘገቡት የኢኮኖሚ እድገት ከዛሬ 6ዓመት ወዲህ የታየ ዝቅተኛ እድገት ነው ። እንደ ዘገባው ነዳጅ አምራች የሆኑ የአፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ እድገት በእጅጉ የሚቀንሰ ሲሆን መካከለኛ ገቢ ያላቸው ከሰሃራ በስተደቡብ የሚገኙ የአፍሪካ ሀገራትም ለአለም የሚያቀርቡት ሸቀጥ ገበያ መቀዝቀዙና እድገታቸውም ከ3.8% እንደማይበልጥ ተመልክቷል።ሆኖም ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው የአፍሪቃ ሃገራት መካከል ኮትዲቯር፣ኢትዮጵያና ታንዛንያ የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ያስመዘግባሉ ብሏል አይ ኤም ኤፍ። እንደ ድርጅቱ በአማካኝ የ7% እድገት ይኖራቸዋል። ናትናኤል ወልዴ ከዋሽንግተን ዲሲ ዝርዝሩን ልኮልናል ።

ናትናኤል ወልዴ

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሀመድ