1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት ባልደራስ»

ረቡዕ፣ መጋቢት 25 2011

የአዲስ አበባ ህዝብ ጥያቄዎች መልስ እንዲያገኙ ጥሪ በቀረበበት በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ምክር ቤቱ ምንም ዓይነት የሥልጣን ጥያቄ እንደሌለው አስታውቋል። ከዚያ ይልቅ የከተማዋ ህዝብ ጥያቄዎች እንዲመለሱ የሚሰራን ፓርቲ እንደሚደግፍ ገልጿል። በሂደትም እስከ እያንዳንዱ ቀበሌ ድረስ በሚዘረጋ መዋቅር እንደሚወከልም አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/3GBpD
Äthiopien PK Addis Abebas Treuhänderrat
ምስል DW/S. Muche

MMT BeriAA Press Conference of Addis Abeba Trustee Council - MP3-Stereo

የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት ባልደራስ የተባለው ስብስብ መሪዎች ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። የአዲስ አበባ ህዝብ ጥያቄዎች መልስ እንዲያገኙ ጥሪ በቀረበበት በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ምክር ቤቱ ምንም ዓይነት የሥልጣን ጥያቄ እንደሌለው አስታውቋል። ከዚያ ይልቅ የከተማዋ ህዝብ ጥያቄዎች እንዲመለሱ የሚሰራን ፓርቲ እንደሚደግፍ ገልጿል። በሂደትም እስከ እያንዳንዱ ቀበሌ ድረስ በሚዘረጋ መዋቅር እንደሚወከልም አስታውቋል። ምክር ቤቱ ባለፈው ቅዳሜ አዲስ አበባ ራስ ሆቴል ዉስጥ ሊሰጥ የነበረዉ ጋዜጣዊ መግለጫ በፀጥታ አስከባሪዎች ተከልክሎ ነበር። መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ወኪላችን ሰሎሞን ሙጬ ተጨማሪ ዘገባ አለው።
ሰሎሞን ሙጬ 
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ