1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የአዲስ አበባ እና የመቀሌ ገዢዎች ዉዝግብ 

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 12 2012

የግጭት መንስኤዎችና መፍትሔያቸዉን የሚያጠናዉ ተቋም እንደሚለዉ የአዲስ አበባና የመቀሌ ገዢዎች ዉዝግብ ሐገሪቱን ወደ ከፋ ቀዉስ ያመራታል ባይ ነዉ

https://p.dw.com/p/3h98v
Äthiopien Militärparade in Tigray
ምስል DW/M. Hailesilassie

የአዲስ አበባና የመቀሌዎች ዉዝግብ፣ የክራይስስ ግሩፕ መፍትሔ

የኢትዮጵያ የፌደራል መንግስትና የትግራይ ክልል መንግስት የገጠሙትን ዉዝግብ ለማስወገድ የዉጪ ሸምጋይ ጣልቃ እንዲገባ ዓለም አቀፉ አጥኚ ድርጅት ክራይስስ ግሩፕ ጠየቀ።የግጭት መንስኤዎችና መፍትሔያቸዉን የሚያጠናዉ ተቋም እንደሚለዉ የአዲስ አበባና የመቀሌ ገዢዎች ዉዝግብ ሐገሪቱን ወደ ከፋ ቀዉስ ያመራታል ባይ ነዉ።አጥኚዉ ቡድን እንደሚለዉ በቅርቡ በምርጫ ሰበብ የተካረረዉን ጠብ ለማስወገድ የወቅቱ የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ሊቀመንበር የደቡብ አፍሪቃዉ ፕሬዝደንት ሲሪያል ራማፎዛ ሽምግልና ቢገቡ ጥሩ ነዉ።የብራስልሱ ወኪላችን

ገበያዉ ንጉሴ 

ነጋሽ መሀመድ

ኂሩት መለሰ