1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዲስ አበባ ዉዝግብ 

ዓርብ፣ መጋቢት 20 2011

የኢትዮጵያ ርዕሰ ከተማ በኦሮምያ መስተዳድር መተዳደር አለባት የሚል ሃሳብ የሚያቀነቅኑና በተቃራኒዉ የከተማይቱ በነዋሪዎችዋ ፍላጎትና ምርጫ መሰረት መተዳደር አለባት የሚል ሁለት የተከፈለ ክርክር እና ዉዝግብ ተጠናቅሮአል። ሁለቱም አክቲቪስቶች እንደሚሉት ከሆነ የአዲስ አበባ ዉዝግብን በዉይይት ለመፍታት ዝግጁ ነን።

https://p.dw.com/p/3FuYw
Kombobild Eskinder Nega und Jawar Mohammed

ሁለቱም አክቲቪስቶች እንደሚሉት ዉዝግቡን በዉይይት ለመፍታት ዝግጁ ነን

የኢትዮጵያ ርዕሰ ከተማ አዲስ አበባ የአስተዳደር ጉዳይ ከፍተኛ የሆነ ዉዝግብ ቀስቅሶአል። ከተማይቱ በኦሮምያ መስተዳድር መተዳደር አለባት የሚል ሃሳብ የሚያቀነቅኑና በተቃራኒዉ የከተማይቱ በነዋሪዎችዋ ፍላጎትና ምርጫ መሰረት መተዳደር አለባት የሚል ሁለት የተከፈለ ክርክር እና ዉዝግብ ተጠናቅሮአል። ዉዝግቡ ዉስጥ ጎላ ብለዉ የሚሰሙት የኦሮሞ ሚዲያ ኔት ወርክ «OMN» ዋና ሥራ አስኪያጅ እና አክቲቪስት ጃዋር መሐመድ እና ጋዜጠኛና የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዉ እስክንድር ነጋ ናቸዉ። ነጋሽ መሃመድ ሁለቱንም አነጋግሮአቸዋል። ሁለቱም አክቲቪስቶች እንደሚሉት ከሆነ ዉዝግቡን በዉይይት ለመፍታት ዝግጁ ነን። በቅድምያ ነጋሽ መሐመድ ከጃዋር ጋር ያደረገዉ ቃለ ምልልስ  ይደመጣል። በመለጠቅ ጋዜጠኛ እና የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዉ እስክንድር ነጋም ዉዝግቡን ማስወገድ የሚቻለዉ በዉይይትና በድርድር እንደሆነ በሰጠዉ ቃለ-ምልልስ አሳዉቋል።  

ነጋሽ መሐመድ 

አዜብ ታደሰ 

ኂሩት መለሰ