1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዲግራት እስርቤት ግድያና ግጭት

ሐሙስ፣ ግንቦት 29 2011

የከተማይቱ ነዋሪዎች፣የሟችና የቁስለኛ ቤተሰቦች እንደሚሉት ግጭቱ የተቀሰቀሰዉ በስፖርት ዉድድር ሰበብ ነዉ።አረና ትግራይ የተባለዉ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ግን በትግራይ ክልል በሚገኙ እስር ቤቶች ዉስጥ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ይፈፀማል ባይ ናቸዉ

https://p.dw.com/p/3Jz9D
Arena Tigray PK  Raya Alamata Unruhen
ምስል DW/M. Haileselassie

የአዲግራት እስርቤት ግድያና ግጭት

 

በትግራይ ክልላዊ መስተዳድር አዲግራት ወሕኒ ቤት ዉስጥ የታሰሩ ታራሚዎችና የወሕኒ ቤቱ ጠባቂዎች ተጋጭተዉ ቢያንስ አንድ እስረኛ ተገደለ፣አራት በፅኑ ቆሰሉ ሌሎች አመለጡ።የከተማይቱ ነዋሪዎች፣የሟችና የቁስለኛ ቤተሰቦች እንደሚሉት ግጭቱ የተቀሰቀሰዉ በስፖርት ዉድድር ሰበብ ነዉ።አረና ትግራይ የተባለዉ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ግን በትግራይ ክልል በሚገኙ እስር ቤቶች ዉስጥ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ይፈፀማል ባይ ናቸዉ።ባለፈዉ ዕሁድ ግጭቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ ቢያንስ አስር የአዲግራት ወሕኒ ቤት እስረኞች ወዳልታወቀ ሥፍራ መወሰዳቸዉንም የፓርቲዉ መሪ አስታዉቀዋል።የወሕኒ ቤቱ አዛዦችና የምስራቃዊ ትግራይ የፀጥታ ኃላፊዎች ስለጉዳዩ ለመናገር ፈቃደኛ ዓይደሉም ወይም አልተገኙም።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ