1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«አዴፓና ሕወሐት መነጋገር አለባቸዉ» ሙሁራን

ረቡዕ፣ ሰኔ 5 2011

የባሕር ዳር እና የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ምሑራን እንደሚሉት የአማራ ገዢ ፓርቲ (አዴፓ)ና የትግራይ አቻዉ (ሕወሐት) የገጠሙት ጠብ የሁለቱን ተጎራባች አካባቢዎች ሕዝብ እያጋጨ ነዉ። ምሑራኑ ለዶይቼ ቬለ እንደነገሩት የፓርቲዎቹ መሪዎች በሽማግሌ፣ በሃይማኖት መሪ እና በስማ በለዉ አማካይነት ከመነጋገር ይልቅ ራሳቸዉ ፊት ለፊት መነጋገር ይገባቸዋል።

https://p.dw.com/p/3KFMH
Äthiopien Axum-Universität in der Region Tigray
ምስል DW/M. Hailesilassie

የአማራና የትግራይ ገዢ ፓርቲዎች ጠብ

የአማራ መስተዳድር እና የትግራይ መስተዳድር ገዢ ፓርቲዎች የገጠሙትን ዉዝግብ  ፊት ለፊት ተነጋግረዉ እንዲያስወግዱ ሁለት ምሑራን መከሩ። የባሕር ዳር እና የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ምሑራን እንደሚሉት የአማራ ገዢ ፓርቲ (አዴፓ) እና የትግራይ አቻዉ (ሕወሐት) የገጠሙት ጠብ የሁለቱን ተጎራባች አካባቢዎች ሕዝብ እያጋጨ ነዉ። ምሑራኑ ለዶይቼ ቬለ (DW) እንደነገሩት የፓርቲዎቹ መሪዎች በሽማግሌ፣ በሃይማኖት መሪ እና በስማ በለዉ አማካይነት ከመነጋገር ይልቅ ራሳቸዉ ፊት ለፊት መነጋገር ይገባቸዋል።

 ዓለምነዉ መኮንን 

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ