1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአጤ ምኒልክ ደብዳቤዎች

ሐሙስ፣ ነሐሴ 5 2003

የአጤ ምኒልክ የደብዳቤ ስብስብን የያዘዉ ሁለት መጻህፍት ባለፈዉ ሰምወን ለአንባብያን ቀርቦአል።

https://p.dw.com/p/RfC8
ምስል picture alliance/dpa

ለአሁንዋ ዘመናዊት ኢትዮጵያ የስልጣኔ በር ከፋች በመሆናቸዉ የሚታወቁት አጤ ምኒልክ የሃይማኖት እና የባህል ተጽኖ ሳይበግራቸዉ ጥበብ በተሞላዉ አስተዋይነት እና ብልህነት አገራቸዉን ያገለገሉ መሆናቸዉን የታሪክ መዛግብት ያሳያሉ። አጤ ምኒልክ በኢትዮጵያ ታሪክ ባርነትን የተቃወሙ፣ የሴቶችን እኩልነት የሚደግፉ የመጀመርያዉ የኢትዮጽያ መሪ እንደነበሩ ሁሉ ታሪክ ይጠቁሙናል። የዳግማዊ አጤ ምኒልክ አድናቂ እንደነበር በተለያዩ ስራዎቹ ያመላከተዉ እዉቁ ጋዜጠኛ እና ደራሲ ጳዉሎስ ኞኞ የአጤ ምኒልክን ደብዳቤዎች አሰባስቦ በማሳተም በታሪክ መዝገብነት ለህዝብ ለማድረስ ያደረገዉ ጥረት በህይወት እያለ ባይሳካለትም ከሁለት አስርተ አመታት በኋላ ዛሪ እዉን መሆኑ በርካታ ኢትዮጵያዉያንን አስደስቶአል። «ይድረስ ለመጽሃፊ አንባቢዎች የተላከ ከጳዉሎስ ኞኞ» ይላል እዉቁ ጋዜጠኛ እና ደራሲ ጳዉሎስ ኞኞ አጤ ምንሊክ በተሰኝዉ መጽሃፉ መቅድም ላይ ያሰፈረዉ ደብዳቤ «እኔ ደህና ነኝ ይህን መጽሃፌን በማቅረቤ በጣም ደስ ብሎኛል። እናንተንም ቢያስደስትልኝ የበለጠ እደሰታለሁ፥ የኢትዮጵያን ታሪክን ስንመለከት ከነገስታቶችዋ ሁሉ አጤ ምኒልክ በዘመናቸዉ በዉጭ አገር የነበረዉን ጥበባዊ ስራ ወደ ኢትዮጵያ ያስገቡ ሰዉ ናቸዉ» ሲል ይጀምራል። ጳዉሎሽ ኞኞ የአጤ ምኒልክን ታሪክ በተለያየ አጋጣሚዎች በማንሳቱ እና ታሪካቸዉን በብዕሩ በመከተቡ አጤ ምኒልክን አድናቂ እንደነበር መገመት አስቸጋሪ አይሆንም። ጳዉሎስ አጤ ምኒልክ በተሰኘዉ በሌላዉ መጽሃፉ በኢትዮጽያ ዉስጥ ለመጀመርያ ግዜ የመጀመርያዋን አዉቶሞቢል የነዱ ምኒልክ በኢትዮጽያ ሹፊሮች ታሪክ ፐርፊክት ድራይቨር የሚለዉን የመጀመርያዉን የመንጃ ፈቃድ የተቀበሉ ምኒልክ ፣የመጀመርያዉን የእህል ወፍጮ የተከሉ ምኒልክ፣ በኢትዮጽያ የመጀመርያዉን ስልክ ያስገቡ ምኒልክ፣ የመጀመርያዉን ብስክሌት መንዳት ተምረዉ የነዱ እና ጣይቱንም ብስክሌት መንዳት አስተምረዉ ሴቶችን ወደ አደባባይ እንዲወጡ የገፋፉ ምኒልክ፣ ሆቴል መብላት ነዉር አለመሆኑን ለማስተማር ሚስታቸዉ ጣይቱን ወጥ-ቤት አድርገዉ መኳንንቱን ሆቴል መብላት ያስተማሩ ምኒልክ መሆናቸዉን እና ሌላም ሌላም አስደናቂ የአጤ ምኒልክን ታሪክ ጳዉሎስ ኞኞ በመጽሃፉ አስቀምጦአል። በቅርቡ በገበያ ላይ የዋለዉ የአጤ ምኒልክ ደብዳቤዎች ስብስብ ጳዉሎስ ኞኞ እጅ እንዴት ደረሰ? ሙሉዉን ቅንብር ያድምጡ!


አዜብ ታደሰ

ሸዋዪ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ