1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፋር የፖለቲካ ፓርቲዎች ዉዝግብና ማስተባበያዉ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 20 2007

የአፋር ነፃ አዉጪ ግንባር (ALF) ከአፋር መስተዳድር ገዢ ፓርቲ ከአፋር ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ)ጋር ያካሄደዉ ዉህደት ህገ ወጥ ነዉ በሚል በዶቼ ቬለ የተላለፈዉ ቃለ መጠይቅ ከሃቅ የራቀ ነዉ ሲል አስተባበለ።

https://p.dw.com/p/1EC3F
Äthiopien Landschaft in Provinz Afar Kamele durch die Wüste
ምስል picture-alliance/dpa


አፋር ነፃ አዉጪ ግንባር ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ከዳ አፎ አይዳ አይስ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ የድርጅቱ ዞን አምስት ሥራ አስፈፃሚ ነኝ ብለዉ ለዶቼ ቨለ ቃለ ምልልስ የሰጡት ግለሰብ ሥራ አስፈፃሚያችን አይደሉም ብለዋል። የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ ድርጅቱ ያካሄደዉ ዉኽደት ሕገ ወጥ ነዉ የሚል ቅሬታ እንዳልቀረበለትና ለዛሬም ዉሳኔ ለማሳወቅ የቀጠረዉ ድርጅትም ሆነ ግለሰብ እንደሌለ ገልፆአል። ዝርዝሩን የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሄር ልኮልናል።

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሄር
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሰ