1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃና የአዉሮጳ ሕብረቶች

ረቡዕ፣ ጥር 15 2011

ፀጥታን በማስከበር፤ ስደተኝነትን በመከላከል ና የምጣኔ ሐብትን በማሳደጉ ረገድ ሁለቱ ማሕበራት እስካሁን ያደረጉት ትብብር አበረታች ዉጤት ማሳየቱን ሚንስትሮቹ አስታዉቀዋል።ለወደፊቱንም  የሁለቱን አሁጉራት ማሕበራት ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ቃል ገብተዋል።

https://p.dw.com/p/3C3pU
Belgien Treffen Außenminister AU und EU in Brüssel
ምስል DW/T. Schauenberg

(Beri Burassels) EU-AU meeting - MP3-Stereo

 ብራስልስ-ቤልጂግ ዉስጥ ለሁለት ቀናት የተደረገዉ የአፍሪቃ እና የአዉሮጳ ሕብረቶች አባል ሐገራት የዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ስብሰባ ትናንት ተጠናቅቋል።ፀጥታን በማስከበር፤ ስደተኝነትን በመከላከል ና የምጣኔ ሐብትን በማሳደጉ ረገድ ሁለቱ ማሕበራት እስካሁን ያደረጉት ትብብር አበረታች ዉጤት ማሳየቱን ሚንስትሮቹ አስታዉቀዋል።ለወደፊቱንም  የሁለቱን አሁጉራት ማሕበራት ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ቃል ገብተዋል።የሁለት ቀኑን ስብሰባ የመሩት የወቅቱ የአፍሪቃ ሕብረት ሊቀመንበር የሩዋንዳዉ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ሪቻርድ ሴ ዜብራና የአዉሮጳ ሕብረት የዉጪ ግንኙነት ኃላፊ ወይዘሮ ፌዴሪካ ሞግሆሮኒ ናቸዉ።

ገበያዉ ንጉሴ 

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ