1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃና የአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ውይይት

ዓርብ፣ ኅዳር 13 2006

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት ሂዩመን ራይትስ ዋች በአንዳንድ የአፍሪቃ ሃገራት በመገናኛ ብዙሃንና በሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች ላይ ተጠናክሮ የቀጠለው ጥቃት እንዲቆም እርምጃ ይወሰድ ዘንድ ብራሰል ቤልጂግ ውስጥ ለተካሄደው የአፍሪቃና የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽኖች የሰብዓዊ መብቶች የጋራ መድረክ አሳስቧል ።

https://p.dw.com/p/1AM73
Stacheldrahtzaun im Konzentrationslager Dachau: Am 21. März 1933 gab Heinrich Himmler die Errichtung eines Konzentrationslagers in Dachau in Auftrag. Damit begann in Dachau ein Terrorsystem, das mit keinem anderen staatlichen Verfolgungs- und Strafsystem verglichen werden kann. Die ersten Häftlinge waren politische Gegner des Regimes, Kommunisten, Sozialdemokraten, Gewerkschafter, vereinzelt auch Mitglieder konservativer und liberaler Parteien. Auch die ersten jüdischen Häftlinge wurden auf Grund ihrer politischen Gegnerschaft in das Konzentrationslager Dachau eingeliefert. In den folgenden Jahren wurden immer neue Gruppen nach Dachau verschleppt: Juden, Homosexuelle, Zigeuner, Zeugen Jehovas, Geistliche u.a. Allein als Folge des Novemberpogroms, der sogenannten Reichskristallnacht, wurden mehr als 10.000 Juden in das Konzentrationslager Dachau gebracht. Insgesamt waren über 200.000 Häftlinge aus mehr als 30 Staaten in Dachau inhaftiert. (Foto vom 25.10.2002)
ምስል picture-alliance / dpa

የአፍሪቃ ህብረትና የአውሮፓ ህብረት በአፍሪቃ ለሰብዓዊ መብት መከበር ለሚታገሉና አውሮፓ ውስጥ ለሚገኙ የውጭ ዜጎች የተጠናከረ ጥበቃ ለማድረግ በጋራ እንዲሰሩ ተጠየቁ ። የአውሮፓ ህብረትም ለውጭ ዜጎችና ለተገን ጠያቂዎች የተሻለ ጥበቃ እንዲያደርግ ጥሬ ቀርቦለታል ። ሂሩት መለሰየአፍሪቃ ህብረትና የአውሮፓ ህብረት ኮሚስዮኖች ብራሰልስ ቤልጅየም ውስጥ ካካሄዱት ዓመታዊ የሰብዓዊ መብቶች ውይይት ዋነኛ ትኩረቶች አንዱ አፍሪቃ ውስጥ በሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች በጋዜጠኖችና በሲቪል ማህበራት ላይ የሚፈፀመው ጥቃት እየከፋና እየተወሳሰበ መሄዱ ነው ። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ወደ አውሮፓ የሚሰደዱ ሰዎች መንገድ ላይ እንዲሁም አውሮፓ ከደረሱ በኋላም የሚያጋጥማቸው ችግርም ሌላው የመነጋገሪያ ርዕስ ነበር ። ለነዚህ ሁለት አብይ ችግሮች የሁለቱ ክፍለ ዓለማት ኮሚስዮኖች የጋራ መፍትሄ እንዲፈልጉ ውይይቱ ከመካሄዱ በፊት ዓለም ዓቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሂዩመን ራይትስ ዋች ጥሪ አቅርቦ ነበር ። ከኮሚስዮኖቹ ስብሰባ አስቀድሞ በተመሳሳይ ርዕስ ላይ በተካሄደው በብራሰልሱ ስብሰባ ላይ የተገኙት በሂዩመን ራይትስ ዋች የአፍሪቃ ክፍል ሃላፊ አቶ ዳንኤል በቀለ በተለይ በብዙ የአፍሪቃ ሃገራት በጋዜጠኞችና በሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በሁለት መንገድ መከላከል ይቻላል ይላሉ ።

Flüchtlinge Afrika Mittelmeer Boot Gefahr
ምስል picture-alliance/dpa

ሂዩመን ራይትስ ዋች እንደሚለው ባለፉት 20 ዓመታት በአንዳንድ የአፍሪቃ ሃገራት መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ቁጥር ማደግና የመገናኛ ብዙሃንም መስፋፋት የሚበረታታ ነው ይሁንና በተለይ ፈላጭ ቆራጭ መንግሥታት ባሉባቸው የአፍሪቃ ሃገራት በመገናኛ ብዙሃንና በሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች ላይ የሚሰነዘረው ጥቃት ተባብሷል ። ስደትን ከሚያባብሱ ምክንያቶች ውስጥ የሚደመሩትን እነዚህን ድርጊቶች የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ ምዕራባውያን መንግሥታት ከማውገዝ ባለፈ በነዚህ ጨቋኝ መንግሥታት ላይ ተጨባጭ እርምጃ ባለመውሰድ ይተቻሉ ። ይህ ጉዳይ የብራሰልሱ የውይይት መድረክ አፅንኦት ሰጥቶት ካነሳቸው ነጥቦች አንዱ ነበር ። አቶ ዳንኤልሰብዓዊ መብትን በመጣስ የተወቀሱት አፍሪቃውያኑ ብቻ አይደሉም ። የአውሮፓ ህብረትም በተለይ ተገን ለሚያሻቸው የውጭ ዜጎች ድንበሩን በመዝጋት ተተችቷል ። ወደ አውሮፓ በባህር ለመሻገር የሚሞክሩ ስደተኞች መንገድ ላይ ችግር ሲያጋጥማቸው አይቶ እዳላየ በማለፍ ብዙዎች ለሞት የሚዳረጉባቸው አጋጣሚዎች በምሳሌነትም ተነስተዋል ። ከመካከላቸው ከአንድ ወር በፊት የኢጣልያዋ ደሴት ላምፔዱዛ አቅራቢያ ከ 350 ሰዎች በላይ ህይወት የጠፋበት አደጋ አንዱ ነው ። አቶ ዳንኤል የአውሮፓ ህብረት በዚህ ረገድ የሚያራምደውን መርህ እንዲመረምር መጠየቁን ተናግረዋል ።

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ