1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃን ቀንድ ያሰጋው ድርቅ

ቅዳሜ፣ ሐምሌ 9 2003

በአፍሪቃ ቀንድ፡ በሶማልያ፡ በኢትዮጵያ፡ በኬንያ፡ በጅቡቲ እና በዩጋንዳ ከአስር ሚልዮን የሚበልጥ ህዝብ አስችኳዩ የምግብ ርዳታ ካልቀረበለት አስከፊ የረሀብ አደጋ እንዳሚያሰጋው ባለፉት ጥቂት ቀናት የወጡ የተመድ ዘገባዎች አስታወቁ።

https://p.dw.com/p/Ra6O
የሶማልያ ስደተኞች በዳዳብ መጠለያ ጣቢያምስል dapd


በዤኔቭ መረጃዎችን ያቀረቡት የርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች ሰራተኞች በተለይ በሶማልያ የተከሰተው ድርቅ እና በዚያ የቀጠለው ውጊያ በሺዎች የሚቆጠሩ የሀገሪቱ ዜጎችን ከቤት ንብረታቸው እንዲሸሹ ማስገደዱን እና በህጻናት ላይ ትልቅ ስጋት መደቀኑን አስጠንቅቀዋል። ስግብግብ ነጋዴዎችም አጋጣሚውን በመጠቀም የምግብን ዋጋ እያስወደዱ ትርፍ ለማካበት የሚያደርጉት ጥረታቸው ችግሩን ይበልጡን እያባባሰው መሄዱንም ገልጸዋል።

አርያም ተክሌ
መሰፍን መኮንን

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ