1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃዉያን ሥደተኞች ችግር በእስራኤል

ዓርብ፣ ግንቦት 2 2005

የእስራኤል መንግሥት በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ እስራኤል ገቡ የሚላቸዉን አፍሪቃዉያን ስደተኞች እያስገደደ ወደየሐገራቸዉ መላኩን ቢያቆምም በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ስደተኞች አሁንም ከእስር ቤት በማይሻል ማቆያ ጣቢያ እየማቀቁ ነዉ።ሳሕሩኒም በሚባለዉ በረሐማ አካባቢ በሚገኘዉ ጣቢያ እንዲሠፍሩ ከተገደዱ ስደተኞች መካካል ሕፃናትና ሴቶች ይገኙባቸዋል

https://p.dw.com/p/18VsV
In this Thursday, May 24 2012, Israelis gather during a demonstration in support of African migrants into Israel. Recent rapes blamed on African migrants have ignited a political and emotional backlash against their ballooning numbers, with Israelis and their leaders stridently and in an alarming new development, violently calling for their expulsion. (Foto:Dan Balitly/AP/dapd).
ምስል dapd



እስራኤል የሚገኙ የአፍሪቃዉያን በተለይም ኤርትራዉያን ሥደተኞች ከፍተኛ በደል እንደሚፈፀምባቸዉ ሥደተኞቹ እና የመብት ተሟጋቾች አስታወቁ።ሥደተኞችና የመብት ተሟጋች ድርጅቶች እንደሚሉት የእስራኤል መንግሥት በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ እስራኤል ገቡ የሚላቸዉን አፍሪቃዉያን ስደተኞች እያስገደደ ወደየሐገራቸዉ መላኩን ቢያቆምም በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ስደተኞች አሁንም ከእስር ቤት በማይሻል ማቆያ ጣቢያ እየማቀቁ ነዉ።ሳሕሩኒም በሚባለዉ በረሐማ አካባቢ በሚገኘዉ ጣቢያ እንዲሠፍሩ ከተገደዱ ስደተኞች መካካል ሕፃናትና ሴቶች ይገኙባቸዋል። ማቆያ ጣቢያ ያልገቡ ሥደተኞችም ሥራ እንዳይሰሩ ይከለከላሉ፥ ይገለላሉም።የሐይፋዉ ወኪላችን ግርማዉ አሻግሬ ዝር ዝር ዘገባ ሎኮልናል።

ግርማዉ አሻግሬ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ