1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃውን ቀንድ ያሰጋው የምግብ እጥረት

እሑድ፣ ሐምሌ 13 2000

« በአፍሪቃ ቀንድ የሚገኙ ሀገሮች መንግስታት ሕዝቦቻቸውን ተደጋግሞ የሚጎዳውን አሳሳቢውን የምግብ እጥረት ችግር ለመቀነስና ከተቻለም ለማስወገድ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት በመውሰድ ሕዝቦቻቸው በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የምግብ ርዳታ ላይ ጥገኛ የሆኑበትን ሁኔታ ማብቃት ይገባቸዋል። »

https://p.dw.com/p/EfbU
ድርቅ የጎዳው የኢትዮጵያ ከፊል
ድርቅ የጎዳው የኢትዮጵያ ከፊልምስል AP

ይህንን የሚሉት ሰሞኑን በዚሁ አካባቢ የተከሰተውን የምግብ እጥረት ሁኔታ ራሳቸው ለመመልከት ከጥቂት ቀናት በፊት ወደ ኢትዮጵያና ወደ ኬንያ ተጉዘው የነበሩት የግብረ ሰናዩ ድርጅት የጀርመናውያንና የላግዘምበርግ የኬር ሊቀመንበር ሄርበርት ሻርምብሩኽ ናቸው።