1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃውያን ስደተኞችመከራ በሊቢያ

ረቡዕ፣ የካቲት 23 2003

ሊቢያ ውስጥ በተቀጣጠለው ሕዝባዊ ዓመጽ የተነሳ በርካታ አፍሪቃውያን በከፍተኛ ሁኔታ መቸገራቸው ተገለፀ። የችግሩ ገፈት ቀማሾች በተለይ ጥቁር አፍሪቃውያን እንደሆኑም ለማወቅ ተችሏል። አፍሪቃውያኑ ከሀዲ በሚል ተፈርጀው የጥቃት ሰለባ እየሆኑ ነው።

https://p.dw.com/p/R5Nq
ምስል DW
ማንተጋፍቶት ስለሺ የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ቃል አቀባይ Jemini Panday ን አነጋግሮ የሚከተለውን አጠናቅሯል። ሊቢያ ውስጥ ቢያንስ 1,5 ሚሊዮን ስደተኞች እንደሚጊኙ በዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ቃል አቀባዩዋ ጄሚኒ ፓንዳይ በተለይ ለዶቼ ቬሌ የአማርኛው ክፍል ገለፁ። ከነዚህ ስደተኞች መካከል ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሀራ በታች ካሉ ህገራት የፈለሱ ስደተኞች በሊቢያ ጥቃት እየተፈፀመባቸው እንደሆነ ይታወቃል። በተለይ ይላሉ ቃል አቀባዩዋ፤ በተለይ ጥቁር አፍሪቃውያኑ በቅጥረኝነት አገልግለዋል በሚል ነው ጥቃት እየተፈፀመባቸው ያለው።