1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃውያን ስደተኞች ተቃውሞ በእስራኤል

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 8 2006

ስደተኞቹ ከተያዙበት ደቡብ እስራኤል ከሚገኘው ባለፈው ሳምንት ከተከፈተው የስደተኞች እስር ቤት ባለፈው እሁድ ሰብረው በመውጣት ከ ሁለት ቀናት በኋላ ዛሬ በኢየሩሳሌም ሰሜን ምዕራብ ዳርቻ ቢደርሱም ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሏቸዋል ።

https://p.dw.com/p/1Abaq
Israel Proteste afrikanischer Migranten in Jerusalem 17.12.2013
ምስል Reuters

አፍሪቃውያን ስደተኖች ዛሬ ኢየሩሳሌም በሚገኘው የእስራኤል ምክር ቤት ክኔሴት ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ ለማካሄድ ያደረጉት ሙከራ ሳይሳካ ቀረ። ስደተኞቹ ከተያዙበት ደቡብ እስራኤል ከሚገኘው ባለፈው ሳምንት ከተከፈተው የስደተኞች እስር ቤት ባለፈው እሁድ ሰብረው በመውጣት ከ ሁለት ቀናት በኋላ ዛሬ በኢየሩሳሌም ሰሜን ምዕራብ ዳርቻ ቢደርሱም ፖሊስ በቁጥጥር ሥር እንዳዋላቸው ግርማው አሻግሬ ከሃይፋ ዘግቧል። የእስራኤል መንግሥት ስደተኞቹን በ48 ሰዓታት ውስጥ ወደ ነበሩበት ማቆያ ካልተመለሱ ወደ ባሰ እስር ቤት እንደሚወረወሩ አስጠንቅቋል። የሃይፋው ዘጋቢያችንን ግርማው አሻግሬን አነጋግረነዋል ።

ግርማው አሻግሬ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ