1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ህብረት እና የዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት ንትርክ

ዓርብ፣ ሐምሌ 3 2001

የዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት የሱዳን ፕሬዚደንት ኦማር ሀሳን ኧል በሺር አንጻር ከጥቂት ወራት በፊት ክስ በመመስረት የእስር ማዘዣም አውጥቶዋል።

https://p.dw.com/p/IlNn
ፕሬዚደንት በሺር በዳርፉርምስል picture-alliance/ dpa
ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት የሱዳን ፕሬዚደንት ኦማር ሀሰን ኧል በሺር በዳርፉር የብዙ መቶ ሺህ ሰው ህይወት ለጠፋበትና እጅግ ብዙዎችም ለተፈናቀሉበት የጦርና በዚያ በስብዕና አንጻር ለተፈጸመው ወንጀል ተጠያቂ ናቸው ይላል። የዓለም አቀፉን ፍርድ ቤት ብያኔ ተግባራዊ ለማድረግ ግን የፍርድ ቤቱን ምስረታ ያስገኘውን የሮሙን ሰነድ የተፈራረሙት ሀገሮች ትብብር አስፈላጊ ነው። ይሁንና፡ ሰነዱን የፈረሙት አፍሪቃውያት ሀገሮች ይህንኑ ትብብር ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም። ምክንያቱ ምንድን ነው? ይህስ ምንስ ሊያስከትል ይችላል?
አርያም ተክሌ