1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ልማት ጉባዔ በጃፓን

ረቡዕ፣ ግንቦት 28 2005

ጃፓን ውስጥ ካለፈው ቅዳሜ አንስቶ እስከ ሰኞ ሶሥት ቀናት የፈጀ የቶኪዮ ዓለምአቀፍ የአፍሪቃ ልማት ጉባዔ ተካሂዷል። በዚሁ አጋጣሚም ጃፓን ግንኙነቷን በማጠናከር በሚቀጥሉት አምሥት ዓመታት ውስጥ 32 ቢሊዮን ዶላር ለአፍሪቃ ልማት ለማቅረብ ወስናለች።

https://p.dw.com/p/18jXy
ምስል picture-alliance/AP Photo

አገሪቱ ከአፍሪቃ ጋር ያላት ግንኙነት ምንም እንኳ ቆየት ያለ ቢሆንም ዛሬ በክፍለ-ዓለሚቱ ላይ በተያዘው ርብርብ ከአዲስ መጤዎቹ ከቻይናና ከሕንድ ጥላ ስር ሆና ነው የምትገኘው። ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንሶ አቤ እንደገለጹት ግን አሁን ጃፓን ታሪካዊ ዕርምጃ ለማድረግ ሳትነሣ አልቀረችም። በጉዳዩ በስኮትላንዱ የዳንዲ ዩኒቨርሲቲ የዓለም ንግድ ጉዳይ ባለሙያ የሆኑትን ዶር/መላኩ ደስታን አነጋግረናል።

መሥፍን መኮንን

ተክሌ የኋላ