1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤ ፍፃሜ

ማክሰኞ፣ ጥር 22 2004

የሶማሊያን የወደፊት ሠላም እንዳይዘነጉ ቢያሳስቡም--- ከጉባኤዉ «ጠብ ያለ ነገር» የለም

https://p.dw.com/p/13tpW
African leaders pose for a group photograph with U.N. Secretary-General Ban Ki-moon during the 18th African Union (AU) summit in Ethiopia's capital Addis Ababa January 29, 2012. REUTERS/Noor Khamis (ETHIOPIA - Tags: POLITICS)
ጉባኤተኞችምስል Reuters

18ኛው የአፍሪቃ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ፤ ባለፈው ሌሊት ተደምድሟል። የኅብረቱን ኮሚሽን አዲስ ፕሬዚዳንት ለመምረጥ ሳይቻል ቀርቶ ፣ ጉንጭ አልፋ ክርክር ጊዜ በመውሰዱ ፤ በመጨረሻ፤ ዣንግ ፒንግና ኮሚሽነሮቻቸው፤ ባሉበት ሥልጣናቸውን እንደያዙ እንዲቀጥሉ ተወስኗል። አንዳንድ ለየት ያሉ ሁኔታዎችም በጉባዔው ተከሥተዋል። ጌታቸው ተድላ ኃ/ጊዮርጊስ-----------------------------------------------------------------------

--------------------------------------------------------------------------------

የአፍሪቃ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ሁነኛ ዉሳኔ ያሳልፍባቸዋል ከተባሉት ጉዳዮች አንዱ የሶማሊያ ሠላምና ሶማሊያ የዘመተዉ የአባል ሐገራት ሠራዊት ነበር።ጉባኤዉ ዘመነ-ሥልጣናቸዉን ለስድት ወራት ያራዘመለቸዉ የሕብረቱ ኮሚሽን ፕሬዝዳት ዣን ፒንግ ለጉባኤተኞች ባቀረቡት ዘገባ ሕብረታቸዉና አባላቱ በሶማሊያ ሠላም ለማስፈን የሚያደርጉት ጥረት ጥሩ ዉጤት ማሳየቱን ጠቅሰዉ ነበር።ይሁንና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ፓ ጊ ሙንን ጨምሮ ጉባኤተኞች የሶማሊያን የወደፊት ሠላም እንዳይዘነጉ ቢያሳስቡም የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ እንደዘገበዉ ከጉባኤዉ «ጠብ ያለ ነገር» የለም።ዝር ዝሩ እነሆ።

ጌታቸው ተድላ ኃ/ጊዮርጊስ-

ታደሰ እንግዳዉ

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የዋኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ