1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ሕብረት ጉባዔ ዐበይት ውሳኔዎች

ሰኞ፣ ጥር 25 2007

የ 90 ዓመቱን የዝምባባዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤን ፤ የወቅቱ ፣ የሕብረቱ ፕሬዚዳንት ይሆኑ ዘንድ የመረጠው የዘንድሮው የአፍሪቃ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ፤ የተለያዩ ጉዳዮችን አንስቶ በመከረበት ወቅት በአንዳንድ ዐበይት ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አስተላልፏል።

https://p.dw.com/p/1EUfq
AU Gipfel in Adis Abeba Äthiopien 2015
ምስል DW/G. Tedla

የበጀት ችግር ያለበት የክፍለ ዓለሙ ዋንኛ ድርጅት ፤ ከአይሮፕላን ቲኬትና ሆቴል ውስጥ የማደሪያ ክፍያ ፣ እንዲሁም በተንቀሳቃሽ ስልኮች ከሚላክ አጭጭር የጽሑፍ መልእክት (SMS) ቀረጥ በማስከፈል 2,5 ቢሊዮን ዶላር መደጎሚያ ለመሰብሰብ አቅዷል። በየአካባቢው ለተፈጠሩ ጦር አማዛዥ ውዝግቦች ፤ ለኢቦላና ለመሳሳሉ ችግሮች መላ ለመሻትም በጥሞና ነው የመከረው። የዶቸ ቨለ የአማርኛው ክፍል ሥራ አስኪያጅ ሉድገር ሻዶምስኪ በዚህ ርእስ ላይ አትቷል።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

አርያም ተክሌ