1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ መሪዎች ጉባኤ

ሰኞ፣ ጥር 24 2002

የአፍሪቃ ኅብረት 14ኛዉ የመሪዎች መደበኛ ስብሰባ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል።

https://p.dw.com/p/Lopc
ምስል AP

ጉባኤዉ የየአገራቱ መሪዎችና ተወካዮች፤ የተመድ ዋና ጸሐፊ፤ የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ማለትም የወቅቱ የአዉሮጳ ኅብረት ፕሬዝደንት፤ የዓለም ባንክ ፕሬዝደንት፤ እንዲሁ የህንድ፤ የካናዳ፤ የኢራንና የሌሎችም አገራት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በተገኙበት ትናንት አዲስ አበባ ላይ ተጀምሯል። ከዚያ አንድ ቀን ቀደም ብሎ፤ አንድ አፍሪቃ የሚለዉን ሃሳብ በሚመለከት የተካሄደዉ ዉይይት ያለ መግባቢያ ተቋጭቷል። ይህ ሃሳብ ከጊዜዉ ቀድሟል በሚሉና የለም አልቀደምም ወቅቱ ነዉ በሚሉ ወገኖች መካከል ዉይይትና ክርክሩ ዛሬም በዝግ መቀጠሉ ተሰምቷል። አፍሪቃን የሚገልፅ አንድ ሰንደቅ ዓላማም ይፋ ተደርጓል።

ታደሰ እንግዳዉ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ