1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ መሪ ሴቶች ጉባዔ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 19 2010

የአፍሪቃ መሪ ሴቶች የመረብ ትስስር በሚል ርዕስ በአፍሪቃ ኅብረት ለሦስት ቀናት የተካሄደዉ ጉባዔ ዛሬ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል። ሴቶችን በይበልጥ በልማቱ ዘርፍ እና በአፍሪቃ የአመራር ደረጃ ለማብቃት ልዉዉጥ በማድረግ በሚጠናከሩበት ላይ የሚሰራ መሆኑ ተገልፆአል። በተመድ ከወራት በፊት የተደረሰ ስምምነት በቀጣይነት የሚሰራ መረብ መሆኑም ተገልፆአል።

https://p.dw.com/p/2wnvh
Äthiopien Addis Abeba Internatonal Women Leaders Net-Working Konferenz
ምስል DW/G. Tedla

«ሴቶችን በልማቱ ዘርፍ እና በመራር ደረጃ ለማብቃት»

የአፍሪቃ መሪ የሴቶች መረብ ትስስር « African Leader  Womens Net-Work»በሚል ርዕስ  ተዋቅሮ ወደ ሥራ ይገባል ተብሎ የታመነበት ከአንድ ወር በፊት ኒዮርክ ላይ በሚገኘዉ በተመድ ዋና ፅፈት ቤት መዋቀሩ ታዉቋል። በአዲስ አበባ በአፍሪቃ ኅብረት ከየአባላቱ የተጋበዙ ሚና ያላቸዉ ሴቶች ወደ ሥራ እንዲገቡ ለማድረግ በመጠናቀቅ ላይ ያለዉ ጉባዔ ዋና መሰረተ ሃሳቡ ነዉ። ይህን በዝርዝር የገለፁት በመንግሥታቱ ጽ/ ቤት ምክትል ፀሐፊዋ አሚና መሃመድ ናቸዉ « ይህ የትስስር መረብ በተጠናከረ መልኩ ተዓማኒነት እንዲኖረዉ በሺዎች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አፍሪካዉያን ሴቶች የሚሳተፉበት መሆን ይገባዋል በቀጣይ በምንገናኝበት ጊዜ ስለሴቶች በጥቅሉ ለማስረዳት አንደበት ይኖረናል። ህልማችን ተግባራዊ በሚሆንበት ለዝያዉ ለተነሳልነት ዓላማ በየሃገራችን የምንሰራበት ተግባር ነዉ የሚሆነዉ። በጋራ የምንወስደዉ አቅዋም የዉይይት መድረክ መከፈት እንደሚያስፈልግ ነዉ። በሃገራቱ መካከልም ሳይቀር አጋርነትና ዓባልነትንም በማካተት የሴቶችን የመሪነት ሚና በማረጋገጥ በልማት በኤኮኖሚዉ ግችትን ቀድሞ መከላከልን በፖለቲካዉ ተሳትፎ ፤ በአፍሪቃም ሴቶችን ከምርጫ በማግለል እየተደረገ ያለዉን በዚህ ሁሉ ላይ ነዉ የምንሰራዉ።»   የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ቦታዉ ላይ ተገኝቶ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል። 

Äthiopien Addis Abeba Internatonal Women Leaders Net-Working Konferenz
ምስል German Embassy Addis Abeba

 

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ