1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ቀንድ ረሐብተኞችና የርዳታ ጥያቄ (ፎቶ 1997)

ዓርብ፣ ሐምሌ 1 2003

አንቶኒዮ ጉተረስ እና አካባቢዉን ለመጎብኘት አዲስ አባባ የሚገኙት የድርጅቱ የሠብአዊ ጉዳይ ምክትል ዋና ፀሐፊ ቫለሪ አሞን ዛሬ አዲስ አበባ ላይ እንዳሉት ጦርነትና ድርቅ ያስከተለዉ ረሐብ ከተገመተዉ በላይ ነዉ

https://p.dw.com/p/RYje
ሶማሊያ-ርዳታ ፈላጊዉምስል dapd


የአፍሪቃ ቀንድን በጣሙን ሶማሊያን የመታዉ ድርቅ ከፍተኛ ሠብአዊ ቀዉስ ማስከተሉ እንደማይቀር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለሥልጣናት አስታወቁ።ደብብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ ዶሎ-ኦዶ መጠለያ ጣቢያ የሠፈሩ የሶማሊያ ስደተኞች የጎበኙት የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር አንቶኒዮ ጉተረስ እና አካባቢዉን ለመጎብኘት አዲስ አባባ የሚገኙት የድርጅቱ የሠብአዊ ጉዳይ ምክትል ዋና ፀሐፊ ቫለሪ አሞን ዛሬ አዲስ አበባ ላይ እንዳሉት ጦርነትና ድርቅ ያስከተለዉ ረሐብ ከተገመተዉ በላይ ነዉ።ታደሰ እንግዳዉ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

ታደሠ እንግዳዉ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ