1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ቀንድ ፈላስያን ተመልካች ጉባዔ በሮም

ሰኞ፣ ኅዳር 22 2007

ባለፈው ሐምሌ ወር ተፈራራቂውን የአውሮፓ ህብረት ጊዜያዊ ሊቀመንበርነቱን የተቀበለችው ኢጣሊያ ፤ በአፍሪቃ ቀንድ ስደተኞችና ፍልሰት ላይ ያተኮረ ስብሰባ ሰሞኑን በሮም ከተማ አካሂዳለች።

https://p.dw.com/p/1Dxo9
Italienisch-Kurs für Flüchtlinge in Palermo, Italien
ምስል DW/B. Riegert

ስብሰባው የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ተወካዮች እና 28 የአፍሪቃ ሀገራት ሚኒስትሮች እና ልዑካንን ያሳተፈ ነበር። ጉዳዩ የአፍሪቃ ቀንድ ሀገራትን እንደመመልከቱም፤ የኢትዮጵያ ፣ የኤርትራ፣ የጅቡቲ እና የሶማልያ ሀገራት ተወካዮች በስብሰባው ተገኝተዋል። የጀርመኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍራንክ ቫልተር ሽታየንማየር « የስደተኞቹን ችግር በጥቂት ሳምንታት ብሎም ወራት ባንዴ የምንፈታው አይደለም ነው ያሉት» የስብሰባውን ይዘት ሮም የሚገኘው ዘጋቢያችን ተክለ እዝጊ ገብረየሱስ ተከታትሎ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል።

ተክለ እዝጊ ገብረየሱስ

ልደት አበበ