1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ኅብረት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 8 2009

ትናንት በብራስልስ የተካሔደው የአውሮጳ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ምክር ቤት ስብሰባ ከአፍሪቃ ጋር በሚኖረው ግንኙነት ላይ እና በአፍሪቃ ቀንድ የፖለቲካ አለመረጋጋት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መክሯል።

https://p.dw.com/p/2d4S5
Russland Federica Mogherini in Moskau
ምስል picture-alliance/dpa/Sputnik/S. Pyatakov

mmt EU ministers on the AU-EU relations & the situation in the HOA - MP3-Stereo

ስብሰባውን የመሩት የአውሮጳ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ወ/ሮ ፌዴሬካ ሞግሔሪኒ ከአፍሪቃ ጋር የሚኖረው ግንኙነት ከተለመደው የእርዳታ ሰጪ እና ተቀባይነት ይልቅ ወደ አጋርነት ማደጉን ገልጠዋል። የፀረ-ሽብር ዘመቻንና ስደተኞችን ለመቆጣጠር  የአዉሮጳ ኅብረት አባል ሃገራት ከአፍሪቃ ኅብረት ጋር በቅርርብ መስራት እንደሚፈልጉ ተገለፀ። የአዉሮጳ ሕብረት አባል ሃገራት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ትናንት ብረስልስ ላይ ባካሄዱት ስብሰባ  የኅብረቱ የዉጭ ጉዳይ ኃላፊ ፌዴሪካ ሞጎገሪኒ ስደተኞች ወደ አዉሮጳ ብቻ ሳይሆን ወደ አፍሪቃ ሃገራትም ይፈልሳሉ ሲሉ ተናግረዋል።በዚህም ምክንያት አዉሮጳና አፍሪቃ ለጋራ ፍላጎት፤ ለተጠናከረ ደኅንነት እንዲሁም የስደተኝነት ምንጭን በጋራ መዋጋት ያስፈልጋል ሲሉ ሞጎሮኒ ተናግረዋል። ብራስልስን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የአፍሪቃ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዝደንት ሙሳ ፋኪ ማሕማት ከወ/ሮ ሞግሔሪኒ ጋር ባወጡት መግለጫ በአይቮሪ ኮስት በሚካሔደው የአውሮጳ እና አፍሪቃ የመሪዎች ጉባኤ ላይ በጋራ እንደሚሰሩ ገልጠዋል። የአቢጃኑ ጉባኤ የወጣቶችን የሥራ እድሎች ማሥፋት በሚቻልባቸው መርኃ-ግብሮች ላይ ያተኩራል ተብሏል። 


ገበያው ንጉሴ 


እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሐመድ