1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ኅብረት ኮሚሽን እጩዎች 

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 3 2009

ባለፈዉ ሳምንት ማለቂያ የአፍሪቃ ኅብረት ኮሚሽን አዲስ ፕሬዚዳንት ለመምረጥ ዉድድር አካሂዶል። ኅብረቱ ተሰናባቿን የኮሚሽኑን ፕሬዚዳንት ድላሚኒ ዙማን ለመተካት ኅብረቱ ዉድድሩን ያካሄደዉ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በዝግ ጉባኤ አልነበረም።

https://p.dw.com/p/2U9JB
AU Kommission Präsidentschaft 5 Kandidaten
ምስል Getachew Tedla HG

 

የቀረቡት አምስት እጩዎች በተዘጋጀላቸዉ መድረክ ራዕያቸዉን በይፋ ያስተዋወቁ ሲሆን የአፍሪቃን መልከዓ ምድርና ቋንቋ መሠረት በማድረግ ሁለት ከእንግሊዘኛ፤ ሁለት ከፈረንሳይኛ እንዲሁም አንድ እጩ ከፖርቱጋል ቋንቋ ተናጋሪዎች እጩዎች ናቸዉ የቀረቡት። የቦትስዋናዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔሎኖሚ ቬንሶን ሞይቶቲ ፤ የቻድ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሳ ፋኪ ማህማት፤ የኤኳቶሪያል ጊኒ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አጋፒቶ ማባ ሞኩዩ ፤ የኬንያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሚና ሞሃመድ እንዲሁም በተመድ የማዕከላዊ አፍሪቃ የቀድሞ ልዩ መልክተኛ እና የሴኔጋል የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር አብዶላዬ ባቲሊ በመድረኩ የየግል ሃሳባቸዉን ለማቅረብ የተፈቀደላቸዉ ሦስት ሦስት ደቂቃ ብቻ እንደነበር በዚህ ዝግጅት ላይ የተገኘዉ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን አመልክቶዋል።


ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ


አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ