የአፍሪቃ ኅብረት ጉባኤና የሠላምና የፀጥታዉ ም/ቤት  

አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:05 ደቂቃ
11.02.2019

በምዕራብ አፍሪቃ የሳሕል ቀጠና ሽብር ተስፋፍቷል

አዲስ አበባ ላይ በመካሄድ ላይ ያለዉ 32ኛዉ የአፍሪቃ ኅብረት መሪዎች ማምሻዉን ያበቃል ተብሎ ይጠበቃል። የአፍሪቃ አገራት የሽብርተኝነትን ሥረ-መሰረት እንዲታገሉ የአፍሪቃ ኅብረት የሰላም እና የጸጥታ ኮሚሽነር ስማኤል ቼርጉይ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታዉቀዋል።

አዲስ አበባ ላይ በመካሄድ ላይ ያለዉ 32ኛዉ የአፍሪቃ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ማምሻዉን ያበቃል ተብሎ ይጠበቃል። ኅብረቱ በ56 ዓመታት ጉዙዉ ለአባል ሃገራቱ እድገት በተለይ በተለያዩ የአፍሪቃ ሃገሮች ተንሰራፍቶ የሚታየዉ ሙስና እንዲያከትም እና የአሕጉሪቱን ወጣቶች በትምህርት ስልጠና በተገቢዉ ደረጃ ማነጽና የሥራ እድልን ለመፍጠር ከሁሉ በቅድምያ በአሕጉሪቱ ሰላም የሚሰፍንበት ጉዳዩ ቅድምያ እንደተሰጠዉ ተመልክቶአል። ይህ የተነገረዉ የአፍሪቃ አገራት የሽብርተኝነትን ሥረ-መሰረት እንዲታገሉ የአፍሪቃ ኅብረት የሰላም እና የጸጥታ ኮሚሽነር ስማኤል ቼርጉይ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በምዕራብ አፍሪቃ የሳሕል ቀጠና ሽብር መስፋፋቱን በተናገሩበት ወቅት ነዉ። አዲስ አበባ ላይ ከሚደረገው 32ኛው የአፍሪቃ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን መግለጫ የሰጡት ቼርጉይ እንደ ቡርኪናፋሱ ያሉ አገራት በየዕለቱ የወንጀለኞች እና የሽብርተኞች የጥቃት ሰለባ መሆናቸውን ተናግረዋል። በአፍሪቃ ኅብረት ጉባኤ በተለይ በሰላምና ደሕንነት ጉዳይ ላይ የተነሱትን ሃሳቦች ይዞ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዝርዝር ዘገባ አዘጋጅቶልናል። 


ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ


አዜብ ታደሰ 
ነጋሽ መሐመድ      
 

ተከታተሉን