1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ኅብረት ጉባኤ ትኩረት

ማክሰኞ፣ ጥር 17 2008

የጉባኤው ትኩረት ሶማሊያ የዘመተው የአፍሪቃ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል ፣የብሩንዲና የደቡብ ሱዳን ጉዳይ እንደሚሆን ተገልጿል ።

https://p.dw.com/p/1HkEu
ምስል Imago

[No title]

26ተኛው የአፍሪቃ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ የፊታችን ቅዳሜ አዲስ አበባ ውስጥ ይጀመራል ። እስከ እሁድ የሚዘልቀው የዚህ ጉባኤ ትኩረትም ሶማሊያ የዘመተው የአፍሪቃ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል ፣የብሩንዲና የደቡብ ሱዳን ጉዳይ እንደሚሆን ተገልጿል ። የህብረቱ አባል ሃገራት አምባሳደሮች ከወዲሁ ባካሄዱት ስብሰባ መሪዎቹ ውሳኔ የሚሰጡባቸው ጉዳይ ላይ ተወያይተው ሰነዶችንም መርምረው አቅርበዋል ። የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ስለ ጉባኤው አጀንዳ የዓለም ዓቀፉ የፀጥታ ጥናት ተቋም በእንግሊዘኛው ምህፃር ISS ባልደረባን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል ።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሒሩት መለሠ

አርያም ተክሌ