1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ አሜሪካ የህክምና ትምህርት ትብብር

ረቡዕ፣ ነሐሴ 2 2004

ዩናይትድ ስቴትስ አፍሪቃ ሀገሮች ዉስጥ የህክምናዉን ዘርፍ ለማሻሻል የምታደርገዉ ድጋፍ ጥራት ላይ ያተኮረ እንደሆነ ተገለጸ። ይህን አስመልክቶም በአዲስ አበባ ለሁለተኛ ጊዜ የአፍሪቃ አሜሪካ የህክምና ትምህርት ትብብር አዉደ ጥናት በመካሄድ ላይ ነዉ።

https://p.dw.com/p/15lx8
ምስል Fistula e.V.

 የህክምና ትምህርት ትብብሩ ዓላማ የህክምና ትምህርት ጥራቱን ማሻሻልና የህክምና ባለሙያዎችን ቁጥር ማሳደግ ሲሆን በአዉደ ጥናቱ ከተለያዩ የአፍሪቃ ሀገሮች የተዉጣጡ ከሶስት መቶ በላይ ባለሙያዎች መሳተፋቸዉን የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ በዘገባ ጠቅሷል። ኢትዮጵያም ከዚህ መርሃግብር ስለሚኖራት ተጠቃሚነት የአዉደጥናቱን አስተባባሪ በማነጋገር ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል። 

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ