1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ አገሮች 100 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ለማልማት አቀዱ

እሑድ፣ ኅዳር 26 2008

አስር የአፍሪቃ አገሮች 31 ሚሊዮን ሔክታር የተራቆተ መሬት መልሶ ለማልማት ቃል ገቡ። ኢትዮጵያን ጨምሮ የአስሩ የአፍሪቃ አገሮች ዓላማ በፓሪስ በሚደረገው የአየር ንብረት ለውጥ ድርድር የቀረበውን 100 ሚሊዮን ሔክታር መሬት መልሶ እንዲያመርት ለማስቻል የቀረበ እቅድ አካል ነው።

https://p.dw.com/p/1HIIR
Kenia Afrika Arid Turkana
ምስል Andrew Wasike

ዛሬ በፓሪስ የጸደቀው ‘አፍሪ 100’ የተሰኘው እቅድ በዓለም ባንክ የአንድ ቢሊዮን ዶላር ይደገፋል። እቅዱን ጀርመንም በገንዘብ የምትደግፍ ሲሆን የግሉ ዘርፍ ደግሞ ተጨማሪ 545 ሚሊዮን ዶላር ያበረክታል ተብሏል። የሩዋንዳው የተፈጥሮ ሐብት ሚኒስትር ቪንሰንት ቢሩታ «መሬታችንን መልሶ ማልማት እድገት ደህንነት እና የሥራ እድል ይፈጥርልናል።» ሲሉ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ፤ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፤ ኬንያ፤ ላይቤሪያ፤ ማዳጋስካር፤ ማላዊ፤ ኒጀር፤ ርዋንዳ፤ ቶጎ እና ዩጋንዳ በእቅዱ የተካተቱ አገሮች ናቸው። እስካሁን የአፍሪቃ መንግስታት የተራቆቱ መሬቶችን መልሶ የማልማት እና አሁን የሚገኙ የደን ይዞታዎችን የከባቢ አየር ለውጥን ለመቋቋምና የበካይ ጋዝ ልቀትን ለመቀነስ በሚያስችል መንገድ ለመጠበቅ የሚያስችሉ 13 ሃሳቦች በፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ አቅርበዋል።

እሸቴ በቀለ

ልደት አበበ