1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ካቶሊካውያን ጳጳሳት ሲኖደስ ጉባዔ ፍጻሜ

ሰኞ፣ ጥቅምት 16 2002

በያዝነው ጥቅምት ወር መግቢያ ገደማ ፣ በሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ዋና ማዕከል በቫቲካን የተጀመረው የአፍሪቃ ካቶሊካውያን ጳጳሳት ሲኖደስ ጉባዔ የተደመደመ ሲሆን፤

https://p.dw.com/p/KFmh
የሞዛምቢኩ ካቶሊካዊ ጳጳስ ዥዋዎ ሲሎታ ፣ የአፍሪቃ ካቶሊካውያን ጳጳሳት የሲኖዶስ ጉባዔ ባለፈው ዓርብ ሲደመደም ፣ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ የተነሱት ፎቶግራፍ፣ምስል AP

በስብሰባው ከ244 የሚበልጡ ካቶሊካውያን ጳጳሳት፣ 33 የአብያተ-ክርስቲያን ሊቃውንትና 29 ታዛቢዎች መሳተፋቸውን ተኽለእግዚእ ገ/የሱስ የላከልን ዘገባ ያስረዳል። የዩናይትድ እስቴትስ ፣ ላቲን አሜሪካ ፣ እስያ፣ ኦሺኒያና አውሮፓ ካቶሊካውያን ርክበ-ጳጳሳትም በዚያው በቫቲካን እንደተገኙ ለአፍሪቃውያኑ የሃይማኖት ተጋሪዎቻቸው፣ የትብብር መልእክታቸውን አሰምተዋል። የተደመደመው የአፍሪቃውያን ካቶሊካውያን ጳጳሳት የሲኖ ዶስ ጉባዔ ዓላማ ምን እንደነበረም ፣ ካቀረቡት አንድ ሃሳብ ጋር በማያያዝ፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካውያን ሊቀ-ጳጳሳት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ተኽለዝጊ ገ/የሱስ

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ