1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚ

የአፍሪቃ የልማት ዕቅድ

ረቡዕ፣ ሐምሌ 3 2011

የአፍሪቃ ሕብረት አባል ሃገራቱን በአንድነት የልማት ጎዳና የሚያስተሳስር ዕቅድ ተልሞ እየተንቀሳቀሰ ነው። በኒያሚ ኒዠር የሚካሄደው የድርጅቱ ጉባኤ በተለይም የኤኮኖሚ እድገትል ለማፋጠን ያስችላል ያላቸውን 14 አነሳሽ ነጥቦች ላይ አትኩሮ እንደሚነጋገር ይጠበቃል።

https://p.dw.com/p/3Ls22
Infografik Karte Verbreitung von Mobilfunkverträgen in Afrika mit Ländernamen DEU

በጋራ የማደግ እቅድ

14 ርዕሰ ጉዳዮች የያዘው አጀንዳ 2063 የተባለው ዕቅድ አፍሪቃን የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚተልም ነው። በአጀንዳው የመሠረተ ልማት ማስፋፋት፤ ትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኒዎሎጂ፣ ባህል እና ሰላም ማስከበር ግንባር ቀደም ጉዳዮች ናቸው። ሌላው የአፍሪቃ ምኞት የነፃ ንግድ ቀጣና መፍጠር ዝግጅት ባለፈው ሳምንት ማለቂያ ላይ ይፋ ሆኗል። ተግባራዊነቱም ከአንድ ዓመት በኋላ ይታያል። በአህጉሪቱ መሪዎች ዘንድ እነዚህ መሠታዊ ጉዳዮች የተስፋፉባት አፍሪቃን የማየት ፍላጎቱ ከፍተኛ ቢሆንም እስካሁን ግን ነገሮች ሁሉ ተስፋ እንደተደረጉት እየተካሄዱ እንዳልሆነ ብዙዎች ያምናሉ። ከምንም በላይ በጦር መሣሪያ የታገዙ እንቅስቃሴዎችን ወደሰላማዊ የውይይት መድረክ የመለወጡ ሥራ ገና ምኑም እንዳልተነካለት የሚናገሩ አሉ። የአፍሪቃ ሕብረትን የ2063 አጀንዳ አስመልክቶ የዶይቼቬለዋ ዚሊያ ካተሪና ፍሮህሊሽ ያጠናቀረችውን የበርሊኑ ዘጋቢያችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል እንደሚከተለው ለዕለቱ የኤኮኖሚው ዓለም አዘጋጅቶታል።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ