1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪካ ህብረትና የሶማሊያ የሰላም ጥረት

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 20 2002

በኡጋንዳ እየተካሄደ ያለው የአፍረካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ በሶማሊያ ተጨማሪ 2000 ጦር እንዲሰማራ ወስኗል። የህብረቱ ዘመቻ ተጨማሪ ሥልጣንም ተሰጥቶታል። ዘመቻው ሰላም ከማስጠበቅ ይልቅ የማስፈን ሃላፊነት ወስዷል።

https://p.dw.com/p/OVrj
የአፍሪካ ህብረትና የሶማሊያ የሰላም ጥረት
ምስል AP

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ ኡጋንዳ ላይ ሲመክር የሶማሊያ ጉዳይ ብዙ ጊዜ ወስዶበታል። በተለይ ከ15 ቀናት በፊት በካምፓላ የተፈጸመው የቦምብ ጥቃት ህብረቱ የሶማሊያን ጉዳይ ለአንዴና ለመጨረሻ እልባት መስጠት እንደሚኖርበት የተገነዘበ መስሏል። በዚህም 2000 ተጨማሪ ወታደሮች እንዲሰማሩ ወስኗል። ይህም በሶማሊያ ያለውን የህብረቱን ጦር ወደ 8000 ከፍ ያደርገዋል ። የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ጂያንግ ፒንግ ለተጨማሪው ጦር ጅቡቲና ጊኒ ድርሻውን እንደሚወስዱ ቃል መግባታቸውን ገልጸዋል። የፖለቲካው ተንታኞች ተጨማሪው ጦር በሶማሊያ የህብረቱን ዘመቻ ከማሳካት አንጻር ሚናው ብዙም የጎላ እንደማይሆን ይናገራሉ። በኡጋንዳ የተሰበሰቡት የአፍሪካ መሪዎች ለሶማሊያው ዘመቻም ተጨማሪ ሥልጣን ሰጥቶታል። የሰላም አስከባሪው ዘመቻ ከዚህ በሃላ ሰላም የማስፈን ስልጣን ወስዷል።

መሳይ መኮንን

ተክሌ የኋላ

ሒሩት መለሰ