1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪካ ህብረት ሚና በዳርፉር

ረቡዕ፣ ኅዳር 28 1998

በዳርፉር የሚገኘዉ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ጦር ለአካባቢዉ መረጋጋት ምን አስተዋፅዖ አደረገ የሚለዉ ከተለያየ ወገን አስተያየት እየተሰጠበት ነዉ። እንደዶቼ ቬለዉ ዘጋቢ ራይንሃርት ባዉምጋርተን እይታ ከሆነ አጋጣሚዉ የአፍሪካ ህብረትን ይዘት የሚያስፈትን ነዉ። በስፍራዉ ተፈናቅለዉ በመጠለያ የሚገኙት የግጭቱ ሰለባዎች የጦሩ መገኘት ከሚፈሯቸዉ ሚሊሻዎች እንዳልታደጋቸዉ ይናገራሉ። የጦሩ አባላት ደግሞ የተኩስ አቁሙን ከማስከበር የዘለለ ኃላፊ

https://p.dw.com/p/E0jH
የእርስ በርስ ጦርነት ባጠቃት ዳርፉር የሚንቀሳቀስ የሱዳን መንግስት ወታደር
የእርስ በርስ ጦርነት ባጠቃት ዳርፉር የሚንቀሳቀስ የሱዳን መንግስት ወታደርምስል AP

�ት አልተሰጠንም ባይ ናቸዉ።

የእርስ በርስ ጦርነት ያዳከማት የሱዳን ምዕራባዊ ግዛት ዳርፉር የአፍሪካ ህብረት ይዘት እና እርምጃ የሚሞከርባት አጋጣሚ ሆናለች።
በስፍራዉም የህብረቱ የሰላም አስከባሪ ጦር መገኘት አፍሪካ የራሷን ችግር ራሷ ለመፍታት የምታደርገዉን ጥረት ያመላክታል ባይ ናቸዉ ታዛቢዎች።
ምንም እንኳን የሞቱት የሰላም አስከባሪ ወታደሮች ቁጥር ቀላል ባይባልም ከመነሻዉ የጦሩ ይዘት ጥሩ ነዉ ተብሎ ተስፋ ተደርጎበታል።
ከስፍራዉ ሰሞኑን የተሰማዉ መልካም ዜና ደግሞ በካርቱም መንግስትና በዓማፂዉ ቡድን መካከል ተቋርጦ የነበረዉ የሰላም ዉይይት መቀጠሉን ያሳያል።
እንደሚታየዉ ግን ግዜዉ በጣም አጭር ነዉ ምክንያቱም የተባበሩት መንግስታት የፀጥታዉ ምክር ቤት የሰጠዉ የጊዜ ገደብ በመጪዉ ታህሳስ 22ቀን ያበቃል። ግልፁን ለመናገር እስከዛሬ ያልተደረሰበት ስምምነት በእነዚህ ቀሪ ቀናት ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት ይከብዳል ይላል የዶቼቬለዉ ዘጋቢ ባዉምጋርተን።
በአካባቢዉ የእርስ በርስ ጦርነት ከተጀመረ ከ1994ዓ.ም. ወዲህ ከአስር ሺ የማያንሱ በከፋ ሁኔታ ሲሞቱ 2ሚሊዮን የሚሆነዉ ህዝብ ከቤት ንብረቱ ተፈናቅሎ በየዛፍ ጥላ ስር ተገን ይዞ ኗሪ ሆኗል።
ሰላም አስከባሪዉ ጦር በስፍራዉ ያጋጠመዉን ዛምቢያዊዉ ጆፍሬ ሃሙሎ የመንግስት ወታደሮች መሆናቸዉን ይናገራሉ የመንግት መሆናቸዉን የምናዉቅበት ምንም አይነት መለያ ሊያሳዩን አልቻሉም። እንደዕኔ ግምት እነዚህ ጃንጃዊድ ናቸዉ ብዬ እጠረጥራለሁ። ሆኖም ሂዜ በመንግስት ወታደሮች ስም ለመከለል የደንብ ልብስ ለብሰዉ መሳሪያ ታጥቀዉ እናያቸዋለን እንዲህ ካለዉ ችግር ጋር ነዉ እየታገልን ያለነዉ ይላሉ።
ጨምረዉም በሽፍትነት በሚጠረጠሩ ወገኖች የከብቶች መሰረቅ ወሬ ከተሰማ ጀምሮ ያለዉ ሁኔታ ተመሳሳይ እንደሆነና የሰላም አስከባሪዉ ጦር የተጠዉ ሃላፊነት የተኩስ አቁም ስምምነቱ ተግባራዊ መሆኑን መቆጣጠር ብቻ መሆኑንም ያስረዳሉ።
5,500 የሚሆነዉን በዳርፉር የሚገኘዉን የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ የሚያዙት ሜጀር ጀነራል ዖኮንኮ ደግሞ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ሙሉ ለሙሉ አላከበሩም በማለት ቅሬታቸዉን ይገልጻሉ።
በተጨማሪም አማፅያኑ የአፍሪካ ህብረት ወታደሮች አስፈላጊዉን ምርመራና አሰሳ ከማድረግ አግደዋል ያ ማለት ደግሞ የሱዳን ነፃ አዉጪ ጦር በእንግሊዝኛዉ ምህፃሩ SLA ነዉ።
የSLA ወታደራዊ ቃል አቀባይ ሞሃመድ ሃሚድ አሊ በበኩላቸዉ የአፍሪካ ህብረቱ ጦር እዚህ ከሰፈረበት ጊዜ ጀምሮ እንደተቸገሩ ይናገራሉ።
እንደቃል አቀባዩ ገለፃ የሰላም አስከባሪ ተብሎ የሰፈረዉ የአፍሪካ ህብረት ጦር በፖለቲካዉ አቋሙ ተቀይሮ ለካርቱም መንግስትoበማድላት ከእነሱ ወገን ታማኝነቱን አጥቷል።
በሌላ በኩል የሱዳን መንግስትም የአፍሪካ ህብረት ሃላፊነት ዓለም ዓቀፍ ጉዳዮቼን እሲጎዳ ድረስ በመዝለዉ ጣልቃ ገብነቱ አላስደሰተኝም ባይ ነዉ።
ኤል ፋሸር የሚገኘዉ የአፍሪካ ህብረት ጦር የፕላን ኃላፊ ሌተናል ኮለኔል ጆሴፍ ዖንዋዳሬ በበኩላቸዉ ጦሩ 90 በመቶ የሚሆነዉን የዳርፉር አካባቢዎች አዳርሷል ስራዉን እየሰራ ነዉ ይላሉ።
ዘምዘም በተሰኘዉ መጠለያ የሚኖረዉ ሞሃመድ ሙሳ እንደሚለዉ ግን ሌት ከቀን በዚያ አካባቢ ሲንቀሳቀሱ ቢያዩም እነሱን የሚያጠቋቸዉን ጃንጃዊድ ሚሊሻዎች ሊያባርሩላቸዉ አልቻሉም።
በእነሱ እምነትም ሚሊሺያዎቹ የሚያድርሱትን የኃይል ጥቃት የሰላም አስከባሪዉ ጦርም ፈርቷል።
በሱዳን የሚገኙ ዓለም ዓቀፍ ታዛቢዎች በበኩላቸዉ የአፍሪካ ህብረት በሙስና የተዘፈቀና ብቃት የሌለዉ ነዉ ሲሉ ይተቻሉ።
ሱዳን የሚገኙት የተባበሩት መንግስታት ልዩ ልዑክይ ጃን ፕሮንክ ደግሞ ዳርፉር ያለዉ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ጦር በተሰለፈበት ግንባር የተዋጣለት ተግባር እየፈጸመ ነዉ በማለት ያሞግሳሉ።