1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪካ እና ሩሲያ ጉባኤ በሶቺ

ሰኞ፣ ጥቅምት 17 2012

በሶቺ ከተማ ባለፈው ሳምንት ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር የመከረችበት የሁለት ቀናት ጉባኤ ተካሒዷል። በጉባኤው የአርባ ሰባት የአፍሪካ አገራት እና የመንግሥታት መሪዎች ተገኝተው በምጣኔ-ሐብታዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

https://p.dw.com/p/3S6Sm
Sotschi Russland-Afrika Gipfel Ägypten
ምስል picture-alliance/dpa/S. Fadeichev

በጉባኤው የኢትዮጵያና የግብጽ መሪዎች መክረዋል።

በሶቺ ከተማ ባለፈው ሳምንት ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር የመከረችበት የሁለት ቀናት ጉባኤ ተካሒዷል። በጉባኤው የአርባ ሰባት የአፍሪካ አገራት እና የመንግሥታት መሪዎች ተገኝተው በምጣኔ-ሐብታዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል። ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከአፍሪካ ጋር ግንኙነትን ማጠናከር ከሩሲያ የውጭ ፖሊሲ ቀዳሚ ዓላማዎች አንዱ መሆን ተናግረዋል።

በጉባኤው ጎን ለጎን ከተካሔዱ እና የዓለምን ቀልብ ከሳቡ ጉዳዮች መካከል የኢትዮጵያው ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታኅ አል-ሲሲ ያደረጉት ውይይት ይገኝበታል።

በውይይቱ መቋጫ ያልተበጀለት እና ሁለቱን አገሮች ለውዝግብ በዳረገው የታላቁ የኅዳሴ ግድብ የውሀ አሞላል እና አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ዐቢይ እና አል-ሲሲ ተነጋግረዋል። በዛሬው የማኅደረ ዜና መሰናዶ የብራስልሱ ገበያው ንጉሴ የጉባኤውን አበይት ጉዳዮች እና የሁለቱ አገራት መሪዎች ያደረጉት ውይይት ላይ ትኩረት አድርጓል።

ሙሉ መሰናዶውን ለማድመጥ መስፈንጠሪያውን ይጫኑ

ገበያው ንጉሴ

አዜብ ታደሰ