1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍንጫ መድማት ወይም ነስር

ማክሰኞ፣ መጋቢት 6 2008

በተለያዩ ምክንያቶች ከአፍንጫ ደም ሊፈስ ይችላል። ነስርየምንለዉ ማለት ነዉ። ብዙዎች መንስኤዉ ምንድነዉ ብለዉ ይጨነቃሉ።

https://p.dw.com/p/1IDN5
28.05.2014 DW Fit und Gesund Nasenbluten

የአፍንጫ መድማት

ነስር ድንገተኛ እና አስደንጋጭ የመሆኑን ያህል አብዛኛዉን ጊዜ ቤት ዉስጥ ሊቆጣጠሩት የሚቻል እንደሆነ አንዳንድ የህክምና ጽሑፎች ይጠቁማሉ። ሆኖም አልፎ አልፎ ደግሞ ብዙ ደም የሚፈስበት ከባድ ነስር ሲያጋጥም የሀኪም ርዳታ ማግኘት አማራጭ እንደማይኖረዉም ያሳስባሉ። የአፍንጫ መድማት ወይም ነስር መንስኤዉ አንድ ብቻ አይደለም፤ የተለያዩ ህመሞች እና ምክንያቶች ሊያመጡት እንደሚችሉ ዶክተር ቶሌራ ወልደየስ የዉስጥ ደዌ ከፍተኛ ሃኪም አስረድተዋል። መንስኤዎቹ የሚጣሩት ችግሩ ያጋጠመዉ ግለሰብ ሃኪም ጋር ቀርቦ በሚደረግ ምርመራ እና ማብራሪያ አማካኝነት ነዉ። እንደሃኪሙ ከሆነ ነስሩ ከፍተኛ ሲሆን ብቻ አይደለም ወደሃኪም መሄድ የሚገባዉ። የሚነስረዉ ሰዉ መንስኤዉን ለማወቅ ከአንገት በላይ ህክምና ባለሙያ ዘንድ ሄዶ በምን ምክንያት ያ እንደተከሰተ መመርመር ይኖርበታል። ነስር በሽታ ነዉ? አንድ ሰዉ ሲነስረዉ በመጀመሪያስ ምን ማድረግ ይኖርበታል? የሃኪሙን ማብራሪያ እና ምክር ለመከታተል የድምጽ ዘገባዉን ይጫኑ።

Nasenbluten
ሲነስር ጎንበስ ብሎ አፍንጫን ቆንጥጦ መያዝምስል Fotolia/O. Schulz

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ