1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢህአዴግ እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች

ረቡዕ፣ የካቲት 8 2009

በውይይቱ የተካፈሉት ፓርቲዎች ለዶቼቬለ እንደተናገሩት በቅድመ ድርድር ሂደት መካተት አለባቸው ያሏቸውን ሃሳቦች በዛሬው ውይይት ላይ አቅርበዋል ።

https://p.dw.com/p/2XcKX
Äthiopien Parlament Hailemariam Desalegn
ምስል DW/Y. G. Egziabher

MMT Beri AA (EPRDF and Opposition parties) - MP3-Stereo

 
ሁለተኛው የኢህአዲግ እና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ውይይት ዛሬ ተካሂዷል ። በዛሬው ውይይት ከየፓርቲዎቹ የቀረቡትን ሃሳቦች ጨምቆ የድርድር እና የውይይት ሰነድ የሚያዘጋጅ ኮሚቴ ተሰይሟል ። በውይይቱ የተካፈሉት ፓርቲዎች ለዶቼቬለ እንደተናገሩት በቅድመ ድርድር ሂደት መካተት አለባቸው ያሏቸውን ሃሳቦች በዛሬው ውይይት ላይ አቅርበዋል ። ሁለቱ ወገኖች ዛሬ የተመረጠው ኮሚቴ በሚያዘጋጀው ሰነድ ላይ ለመወያየት እና ሰነዱንም ለማጽደቅ ለዛሬ ሳምንት ሐሙስ ቀጠሮ ይዘዋል ። ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ከአዲስ አበባ ዝርዝሩን ልኮልናል ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 

ኂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ