የኢሕአዴግ ምክር ቤት መግለጫና አስተያየት
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 9 2011ማስታወቂያ
የግንባሩ ምክር ቤት ጉባኤውን አጠናቅቆ ባወጣው መግለጫ ባለፈው ስብሰባው ያሳለፋቸውን ዋና ዋና ያላቸውን ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች መሠረት በማድረግ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት ተጨባጭ ርምጃዎች ሲወሰዱ መቆየታቸውን በዚህ ስብሰባው በዝርዝር መመልከቱን ጠቅሷል። ከዚህም ሌላ ምክር ቤቱ በእህት ድርጅቶችና በአመራሩ መካከል የሚታየውን መጠራጠር በመፍታት የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ማምጣት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከሩንም አመልክቷል። የምክር ቤቱ መግለጫ አክሎም የኤኮኖሚ ይዞታውን፤ እንዲሁም የመገናኛ ብዙሃን አዘጋገብን የሚመለከቱ ጥቅል ሃሳቦችንም አንስቷል። በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህሩ ረዳት ፕሮፌሰር ዳንኤል መኮንን መግለጫው ወትሮም የሚታወቀው ኢህአዴግ አለመለወጡን ያሳያል ይላሉ። መግለጫውን መነሻ በማድረግ አስተያየታቸውን ጠይቄያለሁ።
ሸዋዬ ለገሠ
ማንተጋፍቶት ስለሺ