1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢራቁ ጦርነት እና የአሜሪካዉ የጥናት ዘገባ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 2 1999

በኢራቅ እ.አ 2003 የነበረዉ ጦርነት ያስከተለዉ መዘዝ ለ650,000 ህዝቦች ሰለባ እንደሆነ አንድ መንግስታዊ ያልሆነ የአሜሪካ መርማሪ ድርጅት አስታወቀ

https://p.dw.com/p/E0hw

ይህ ጥናታዊ ጽሁፍ በትናንትናዉ እለት The Lancet የተባለዉ የብሪታንያዉ መጽሄት በህክምና ድህረ-ገጹ ላይ ነበር በይፋ ያወጣዉ። የአሜሪካዉ የጥናት ቡድን እንደሚያመለክተዉ በኢራቅ ጦርነቱ ከተጀመረ ከዛሪ ሶስት አመት ተኩል ጀምሮ እስከ ያዝነዉ አመት የጦር ወታደሮችንም ሆነ፣ ሲቢል ማህበረሰባትን ጨምሮ 650,000 ህዝብ ማለቃቸዉን ያሳያል። ከእነዚህ ህዝብ መካከል 600,000 ዉ በጦርነቱ ሰበብ፣ አልያም ታፍነዉ የተወሰዱ እና በስቃይ የተገደሉ ናቸዉ። 50,000 ያህሉ ህዝብ ደግሞ በጦርነቱ ሰበብ የቆሰለ እና በመድሃኒት እጦት ምክንያት በበሽታ ህይወቱን ያጣ ነዉ። የጥናቱ ጽሑፍ በመቀጥል በአሁኑ ወቅት በኢራቅ ባለዉ ዉጥረት እና ግጭት በቀን ዉስጥ ብቻ 500 ያህል ሰዉ ይሞታል። ይህ ቁጥር የሚያሳየዉ በኢራቅ ጦርነቱ ከተጀመረበት ግዜ ጀምሮ የሚሞተዉ የህዝብ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እንደጨመረ ነዉ ።

አሰቃቂ የሆነ ሃቅ! የቡሽ መንግስት እስካሁን በኢራቁ በጦርነቱ 30,000 ሺ ህዝብ አልቋል ሲል የብሪታንያዉ ጥናት ደግሞ 50,000 ያህል ብቻ እንዳለቀ ነዉ ግምቱ። እዉነታዉ ግን 650,000 ህዝብ እና ከዚያም በላይ ማለቁ ነዉ። በአሜሪካ በጣም ታዋቂነት እና ተቀባይነት ያለዉ የሜሪላንዱ Johns Hopkins ዪንቨርስቲ ዉስጥ ያሉ ተመራማሪ ዶክተሮች ይህንን ጥናታቸዉን ለአሜሪካ ህዝብ ካቀረቡ በኻላ፣ ጆርጅ ደብሌዉ ቡሽ ይህ የተጠቀሰዉ የጥናት ቁጥር የማይታመን ነዉ ሲሉ ነቀፌታቸዉን ያሰሙት። ቡሽ ይህንኑ ንግግራቸዉን አስታከዉ በኢራቅ ዉስጥ በየቀኑ የሚደርሰዉን ጥፋት እና ብጥብጥ ለመግታት አዲስ ታክቲክ እንደሚጠቀሙ ነበር ተናገሩት። ይኸዉም ይላሉ ቡሽ እስካሁን የተጠቀምነዉ ዘዴ መፍትሄ ካላመጣ፣ ታክቲካችንን መቀየር ይኖርብናል! በአሁኑ ወቅት መንግስታቸዉ ጦሩን ከኢራቅ እንደማያወጣም ነዉ በግልጽ ያስቀመጡት።
The Lancet የብሪታንያዉ የጤና ጽሑፍ በድህረ-ገጹ ይፋ ያደረገዉ የአሜሪካዉያኑ የጥናት ዘገባ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶታል። ጥናቱ Cluster sampling በኢራቅ በተከለሉ ቦታዎች በርካታ ናሙና በመዉሰድ ያለዉን የነፍስ ጥፋት በማየት፣ የሞቱን መንስኤ መርምሮ ካለዉ ነባራዊ ሁኔታ በአገሪቷ ያለዉን ጥፋት በማጠቃለል አቅርቦአል።
በአሜሪካም የጥናቱ ነቃፊዎች በመጀመርያ ደረጃ ስለቀረበዉ የጥናት መልስ ምንም አይነት ጥርጣሪ ባይኖራቸዉም ጥናቱ ተጋኖ ቀርቧል ማለታቸዉን ከመግለጽ ወደኻላ አላሉም። በተለይም ቅራኒያቸዉ ከአራት ሳምንታት በኻላ በአሜሪካ ከሚካሄደዉ የካቢኔ ምርጫ በፊት ይህ ጥናት መዉጣቱ አስቆጥቷቸዋል። እንዲህ አይነቱ ዜና የቡሽን መንግስት በምርጫዉ ሰአት ድምጽ ያሳጣዋልና።
በኢራቅ በተለይ በባግዳድ ተጨማሪ ወታደሮች ቢሰማሩ ምናልባትም በቦታዉ ላለዉ ችግር መፍትሄ ይሆናል። ነገርግን የአሜሪካ ህዝብ ስለጦርነት መስማት ሰልችቶታል በአሜሪካ ዉስጥ ወደ ኢራቅ ተጨማሪ ወታደሮች ለመላክም ሆነ፣ በኢራቅ ጉዳይ ዙርያ ያለዉ ፖለቲካ ሁኔታ ገና ግልጽ አይደለም። በኢራቅ ያሉ የአሜሪካ ወታደሮችም ቢሆኑ በኢራቅ ሰላምን ለማስፈን የሚችሉትን ሁሉ አሳይተዉ የተረጋጋች ኢራቅን ለማምጣት ካቅማቸዉ በላይ ሆኖባቸዋል።