1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢራቅ መንግስት ሞሱልን መቆጣጠሩን አስታወቀ

እሑድ፣ ሐምሌ 2 2009

የኢራቅ መንግስት ራሱን እስላማዊ መንግስት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ጠንካራ ምሽግ ነው የሚባለውን የሞሱልን ከተማ ነጻ መውጣቱን ይፋ አደረገ፡፡ የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይደር አል አባዲ ሞሱል ድረስ በመጓዝ ወታደሮቻቸውን “እንኳን ደስ አላችሁ” ብለዋል፡፡ 

https://p.dw.com/p/2gEAj
Irak, Rückeroberung von Mossul vom IS
ምስል Reuters/A.Saad

የኢራቅ መንግስት የሞሱል ከተማን በድጋሚ ለመቆጣጠር ዘመቻ የከፈተችው ባለፈው ጥቅምት ወር ነበር፡፡ የኢራቅ ጦር ስድስተኛ ክፍለጦር መሪ ሌተናል ጃሲም ኒዛል እንደተናገሩት የእርሳቸው ወታደሮች ድል አድርገዋል፡፡ ወታደሮቹ በታንኮች ላይ ሆነው ድላቸውን  በዳንስ እና በዘፈን በሚገልጹበት ወቅት በአቅራቢያቸው የአየር ጥቃት መቀጠሉን አሶሴትድ ፕሬስ ከስፍራው ዘግቧል፡፡ እንደ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገባ ጠቅላይ ሚኒስትር አባዲ የሞሱልን በድጋሚ በቁጥጥር ስር መዋል ለማወጅ በቦታው በተገኙት ወቅት እንኳ ውጊያ ይካሄድ ነበር፡፡ 
በሞሱል በመንግስት ወታደሮች እና ታጣቂዎቹ መካከል ወራትን የፈጀው ከባድ ውጊያ በርካቶችን ለሞት የዳረገ ሲሆን 900 ሺህ ገደማ ነዋሪዎችን ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሏል፡፡ የሞሱል አብዛኛው ክፍል እና በዙሪያ ገባው ያሉ አካባቢዎቹን በውጊያው መውደማቸውን የዜና ዘገባዎች ጠቁመዋል፡፡ 

ተስፋለም ወልደየስ

ልደት አበበ