1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢራቅ ሴቶች የመብት ይዞታ

ረቡዕ፣ ሰኔ 24 2001

ኢራቅ የሴቶችን ሰብዓዊ መብቶች የሚያስከብር ህግ ፈራሚ አገር ብትሆንም በእነሱ ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች ቁጥር አልቀነሰም።

https://p.dw.com/p/IeNu
ሃዘን ያቆራመዳቸዉ ኢራቃዉያን ሴቶችምስል AP

አገሪቱ ከገባችበት ጦርነት፤ የአጥፍቶ ጠፊዎች ጥቃትና ቀደም ብሎም ከተጣለባት ማዕቀብ የተነሳ ወንዶቹ ለጭንቀት መጋለጣቸዉን የሚናገሩት የሴቶች ጉዳይ ተመራማሪዎች፤ እንደሚሉት የዚህ ሁሉ ችግር ማረፊያ ደግሞ ሴቶቹ ናቸዉ። ልጆችና ባሎቻቸዉን በጦርነትና ጥቃቶች ማጣታቸዉ የቤተሰብ ኃላፊነትን እነሱ ላይ ጥሏል። ምንም እንኳን የተሻለ ነፃነት ለሴቶች የማምጣት ዓላማ እንዳላቸዉ የሚገልፁ ወገኖች ቢኖሩም በተግባር እጅግም የታየ ነገር እንደሌለ ነዉ የሚገለፀዉ።

ሸዋዬ ለገሠ/ተክሌ የኋላ