1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢራን ኑክሌር መ/ግብር ድርድር

ሐሙስ፣ የካቲት 29 2004

እስራኤል የኢራንን የኑክሌር ተቋማት ለመደብደብ ያዙኝ ልቀቁኝ እንዳለች፥ዩናይትድ ስቴትስ የእስራኤልን ዛቻ እያጦዘች እንዳረገበች፥ ኢራን መራሐ-ግብሯን እንዳሰፋች፥ አዉሮጳ እና

https://p.dw.com/p/14GUo
An Iranian flag flutters in front of the reactor building of the Bushehr nuclear power plant, just outside the southern city of Bushehr, Iran, Saturday, Aug. 21, 2010. Iranian and Russian engineers began loading fuel Saturday into Iran's first nuclear power plant, which Moscow has promised to safeguard to prevent material at the site from being used in any potential weapons production. (ddp images/AP Photo/Vahid Salemi)
የኢራን የኑክሌር ተቋምምስል dapd

07 03 12


አሜሪካ ማዕቀብ እንደጣሉ ትናንት ላይ ሲደረሱ የጀርመኑ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ጊዶ ቬስተርቬለ እንዳሉት የድርድር ተስፋዉ ዳግም ፈነጠቀ። በኢራን የኑክሌር መርሐ ግብር ሰበብ የተቀሰቀሰዉን ዉዝግብ ለማስወገድ የሚደረገዉ ድርድር እንዲቀጥል ኢራን ያቀረበችዉን ጥያቄ የአዉሮጳ ሕብረት ትናንት በይፋ ተቀብሎታል።የሕብረቱ የዉጪ ግንኙነት ሐላፊ ካትሪን አሸተን ትናንት እንዳስታወቁት ሰባት መንግሥታት የሚወከሉበት ድርድር እንዲቀጥል ቴሕራን ያቀረበችዉን ሐሳብ ሕብረታቸዉ ተቀብሎታል።ኢራን በአንድ ወታደራዊ ሠፈር የሚገኝ የኑክሌር ተቋሟን የዓለም የአቶም ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን (IAEA) ባለሙያዎች እንፈትሹትም ፈቅዳለች።ሌዎን ሽቴበ የዘገበዉን ነጋሽ መሐመድ አጠናቅሮታል።


ድርድሩ ኢራን፥ዩናይትድ ስቴትስ፥ ሩሲያ፥ቻይና፥ ብሪታንያ፥ ፈረንሳይ እና ጀርመን የሚወከሉበት የሰባትዮሽ፥-አዘጋጅ-አመቻቺዉ ደግሞ የአዉሮጳ ሕብረት ነዉ። ያለፈዉ አንድ አመት ከምናምን ግን ለቴሕራንና ለብራስልስ ድርድሩ ተቋርጦ ዉዝግባቸዉ፥ የሰላም ተስፋቸዉ ቆሞ-ማዕቀብ-ብቀላቸዉ የነገሰበት ጊዜ ነዉ።ኢራን የኑክሌር መርሐ ግብሯን ማሳደግዋን ስታሳዉቅ፥ የአዉሮጳ ሕብረት ደግሞ በማዕቀብ ላይ ማዕቀብ ሲጥልባት፣-አመቱ ዞሮ ገጥሞ ከሁለተኛዉ አንድ ሁለት ወር አነሳ።

እስራኤል የኢራንን የኑክሌር ተቋማት ለመደብደብ ያዙኝ ልቀቁኝ እንዳለች፥ዩናይትድ ስቴትስ የእስራኤልን ዛቻ እያጦዘች እንዳረገበች፥ ኢራን መራሐ-ግብሯን እንዳሰፋች፥ አዉሮጳ እና አሜሪካ ማዕቀብ እንደጣሉ ትናንት ላይ ሲደረሱ የጀርመኑ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ጊዶ ቬስተርቬለ እንዳሉት የድርድር ተስፋዉ ዳግም ፈነጠቀ።

«ኢራን ቁም ነገር ወዳለዉና ከልብ ወደመነጨ ፖለቲካዊ ድርድር ከተመሠለሰች፥(ለዉዝግቡ) ዲሞሎማሲያዊና ፖለቲካዊ መፍትሔ መፈለጉ አይገድም ብለን እናምናለን።»

ይሕ በትክክል የምዕራባዉያኑ ጥያቄ ነዉ።የኢራን መሪዎች ዘጋቢ ሌዮን ሽቴበ እንደፃፈዉ ጊዜ ለመግዛት ይሞክራሉ።ተቆጣጣሪዎች ወደ ሐገራቸዉ እንዳይገቡ ከልክለዉም ነበር።በየጊዜዉ የሚደረገዉ ድርድር ለመስተጓጎሉ ኢራንን ተጠያቂ የሚያደርገዉ ዘጋቢዉ፥ኢራኖች የራሳቸዉን ፍላጎት ካልሆነ በስተቀር ሰትጥቶ ለመቀበልም ብዙም ፍላጎት የላቸዉም ባይ ነዉ።የአዉሮጳ ሕብረት የዉጪ ግንኙነት የበላይ ካትሪን አሽተን ግን ተስፋ አላቸዉ።

«ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብን የሚያሳስበዉን የኑክሌር መርሐ-ግብር በተመለከተ ከኢራን ጋር ገንቢ ድርድር እናደርጋለን የሚል ተስፋ አለን።በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ዕለቱንና ሥፍራዉን እንወስናለን።»

የአዉሮጳ ሕብረትና ዩናይትድ ስቴትስ ከጥርጣሬ፥ አንዳዴ ከዛቻ ጋርም ቢሆን የኢራንን የኑክሌር ዉዝግብ ለማስወገድ የዲፕሎማሲያዊ በር አልተዘጋም ባዮች ናቸዉ።የእስራል መንግሥት ግን ባለፉት ሳምንታት ኢራንን ለመደብደብ በተደጋጋሚ እንደዛተ ነዉ።ዛቻ ፉከራዉ የድርድሩን ሒደት ሊያከብደዉ ይችላል።ወይም በተቃራኒዉ በተደራዳሪዎች ላይ ተፅዕኖ አሳርፎ ከጥሩ ዉጤት ያደርሳቸዉ ይሆናል።የጀርመኑ ወጪ ጉዳይ ሚንስትር ጊዶ ቬስተር ቬለ ግን ወታደራዊ እርምጃ ከአካባቢዉ አልፎ ለአለም ሠላምና ፀጥታ አስጊ ነዉ ባይ ናቸዉ።

«ይሕ፥ የአካባቢዉን ፀጥታ ይበልጥ የሚያደፈርስ አደጋ ብቻ ሳይሆን፥ የአለም አቀፉን የፀጥታ-ሥርዓት የሚያመሰቃቅል በሆነ ነበር።ከዚሁ ጋር ልንገነዘበዉ የሚገባን ነገር (ድብደባዉ) ወትሮም በቋፍ በሚገኘዉ በዚያ አካባቢ የኒክሌር ጦር መሳሪያ እሽቅድምድም ሊያስከትል ይችላል።»

አዲሱ ድርድር ከፈጠነ መጋቢት አጋማሽ ይጀመራል ተብሎ ነዉ የሚጠበቀዉ።ከመጀመሪያዉ ዙር ድርድር ሁነኛ ዉጤት ይገኛል ብሎ የሚጠብቅ ግን የለም።

ነጋሽ መሐመድ
ተክሌ የኋላ

Director General of the International Atomic Energy Agency, IAEA, Yukiya Amano of Japan casts a shadow on the wall during a news conference after a meeting of the IAEA's board of governors at the International Center, in Vienna, Austria, on Monday, March 5, 2012. Amano spoke to the 35-nation IAEA board amid backdoor diplomatic maneuvering aimed at coming up with substantial joint pressure on Iran to end its nuclear defiance and address global concerns about its nuclear activities. (Foto:Ronald Zak/AP/dapd)
ድርድሩምስል dapd
FILE - In this Tuesday, April 8, 2008 file photo released by the Iranian President's Office, Iranian President Mahmoud Ahmadinejad, center, visits the Natanz Uranium Enrichment Facility some 200 miles (322 kilometers) south of the capital Tehran, Iran. The village of Fordo _ which is hailed by Iranians for the greatest per capita losses during the 1980s war with Iraq _ was chosen to symbolize Iran's next move in its nuclear brinksmanship: An underground uranium enrichment site that could begin operations by early next year.(AP Photo/Iranian President's Office, File)
የኢራን ፕሬዚዳንት ጉብኝትምስል AP Photo/Iranian President's Office
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ