1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢራን የአቶም መረሃ-ግብር ስምምነት

እሑድ፣ ኅዳር 15 2006

የኃያላኑ መንግሥታት ልዑካንና የኢራን ተወካዮች በኢራን የኒዩክልየር መርሃ ግብር ላይ ጄኔቫ ላይ የጀመሩት ድርድር ይሁንታ መልስን አግኝቶ መጠቃለሉ ተነገረ። አሁን የተደረሰዉ ስምምነት ከኢራን ጋር መፍትሄ ለመድረስ የሚያስችለን ዋና መሰረታዊ ጭብጥ ነዉ ሲሉ፤

https://p.dw.com/p/1ANF8
European Union foreign policy chief Catherine Ashton (3rd L) delivers a statement during a ceremony next to British Foreign Secretary William Hague, Germany's Foreign Minister Guido Westerwelle, Iranian Foreign Minister Mohammad Javad Zarif, Chinese Foreign Minister Wang Yi, U.S. Secretary of State John Kerry, Russia's Foreign Minister Sergei Lavrov and French Foreign Minister Laurent Fabius (L-R) at the United Nations in Geneva November 24, 2013. Iran and six world powers reached a breakthrough agreement early on Sunday to curb Tehran's nuclear programme in exchange for limited sanctions relief, in a first step towards resolving a dangerous decade-old standoff. REUTERS/Denis Balibouse (SWITZERLAND - Tags: POLITICS ENERGY) (eingestellt von qu)
ምስል Reuters

ድርድሩን ሲመሩ የነበሩት፤ በፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ዉስጥ ድምፅን በድምፅ የመሻር ሥልጣን ያላቸዉ አምስቱ ሐያላን ሀገራትና የጀርመኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዶ ቬስተርቬለ እንዲሁም፤ የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ካትሪን አሽተን ገልፀዋል። ከጥቅምት ወር ወዲህ ለሶስተኛ ጊዜ በተካሄደዉ በዚሁ ንግግር ኢራን ዩራንየም በከፍተኛ ደረጃ ከማብላላት እንድትቆጠብ በምትኩም ምዕራቡ ዓለም የጣለባትን የኤኮኖሚ ማዕቀብ ለጊዜው እንዲያላላ የታሰበ እንደነበር ተመልክቷል። ከሁለት ሳምንት በፊት ኢራንና አምስቱ የተመድ ፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት አባላት እንዲሁም ጀርመን ባካሄዱት ንግግር ኢራን 20 ከመቶ የደረሰውን ዩራንየም የማብላላት ደረጃዋን ወደ 3.5 በመቶ ዝቅ እንድታደርግ በሚጠይቀው ውል መስማማት ተስኗቸው መለያየታቸዉ ይታወሳል። በዉይይቱ አኳያ ከኢራን ወገን እንደተገለፀዉ፤ ሀገሪቱ ከምታካሂደዉ የአቶም መረሃ-ግብር አንዱን ክፍል ታቆማለች። ለዚህም በኢራን ላይ የተጣለዉ ዓለም አቀፍ ማዕቀብ ይነሳል ተብሏል። እንደ ኢራኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሃመድ ዣዋድ ሻሪፍ ትንተና በተደረሰዉ ስምምነት ላይ፤ ኢራን የምታመርተው ፕሉቶንየም ተቀባይነት ያገኘ ግን፤ ሀገሪቱ በሚቀጥሉት ስድስት ወራቶች የምታብላላዉ የፕሉቶንየም መጠን ከአምስት በመቶ በልጦ መገኘት የለበትም። የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ከዋይት ሃዉስ በሰጡት መግለጫ፤ በአቶም ጉዳይ የተነሳን ጭቅጭቅ እስከ መጨረሻዉ ለማወገድ፤ ስምምነቱ እጅግ ወሳኝ እርምጃ ነዉ ሲሉ ገልጸዋል። ከአደራዳሪዎቹ መካከል አንዱ የሆኑት የጀርመኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዶ ቬስተርቬለ በበኩላቸዉ፤ ኢራን የአቶም መሣርያን ተጠቃሚ እንዳትሆን፤ ወሳኝ ከሆነዉ የዓላማ መዳረሻ ላይ ተቃርበናል ብለዋል።
የዓለም ኃያላን መንግሥታት፤ አራን በሚገኘው ማብላያ የሚመረተው ፕሉቶንየም እንዲሁም 20 በመቶ ዩራንየም ለኒዩክልየር ጦር መሣሪያዎች ማምረቻነት ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላል የሚል ስጋት ያላቸዉ ሲሆን፤ምዕራባዉያን ሀገራት፤ ኢራንኑክሌር ቦምብ ትሰራበታለች ብለዉ የሚጠረጥሩትን የኑክሌር መርሐ ግብሯን ባለማቋረጧ ተደጋጋሚ ማዕቀብ ጥለዉባት ቆይተዋል። የቴህራን መንግሥት በበኩሉ ወቀሳውን ሀሰት በማለት፣ የአቶም መረሃ -ግብሩ ለሠላማዊ የኃይል ምንጭ ተግባር ጥቅም ላይ እንደሚያዉል በተደጋጋሚ ሲገልፅ መቆየቱ ይታወቃል።

አዜብ ታደሰ

ልደት አበበ

(L-R) Germany's Foreign Minister Guido Westerwelle, British Foreign Secretary William Hague, Chinese Foreign Minister Wang Yi, U.S. Secretary of State John Kerry, French Foreign Minister Laurent Fabius, Russia's Foreign Minister Sergei Lavrov, EU foreign policy chief Catherine Ashton and Iranian Foreign Minister Mohammad Javad Zarif gather at the United Nations Palais in Geneva November 24, 2013. Iran and six world powers reached a breakthrough deal early on Sunday to curb Tehran's nuclear programme in exchange for limited sanctions relief, in what could be the first sign of an emerging rapprochement between the Islamic state and the West. REUTERS/Carolyn Kaster/Pool (SWITZERLAND - Tags: POLITICS ENERGY)
ምስል Reuters