1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢራን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ፣

ሐሙስ፣ ሰኔ 4 2001

46 ሚልዮን ከሚገመተው የኢራን ህዝብ መካከል፣ ለምርጫ ብቁ የሆኑት 65 ከመቶ ሲሆኑ፣ የ 10ኛውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት ነገ ይወስናሉ።

https://p.dw.com/p/I7dy
ምርጫ በኢራን፣ምስል ILNA

በእጩነት የቀረቡት ተወዳዳሪዎች ፣ በኢራን አብዮት ከፍተኛ ተሳትፎ የነበራቸውና በአገሬው ህዝብ ዘንድ የተከበሩ በመሆናቸው፣ ውድድሩን ጠንካራ ሊያደርገው እንደቻለ ፣ የፖለቲካ ታዛቢዎች ይናገራሉ። ከ 4ቱ ተወዳዳሪዎች መካከል ዋንኞቹ ፕሬዚዳንት ማህሙድ አህማዲነጃድና የቀድሞው ጠ/ሚንስትር ሚር ሁሴን ሙሳቢ ሲሆኑ፣ ሁለቱ፣ በቴሌቭዥን ባደረጉት ክርክር ፣ በውጭ ግንኙነት፤ በኑክልየር ፣ በማኅበራዊ ኑሮ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮሩ ሲሆን፣ የ «ምረጡን» ዘመቻ ባካሄዱባቸው 4 ሳምንታትም ፤ ደጋፊዎቻቸው አደባባይ በመውጣት የቅስቀሳው ተሳታፊዎች ሆነዋል።

---ነቢዩ ሲራክ---

ተክሌ የኋላ/ሸዋዬ ለገሠ