1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮዽያ መንግስት የድርድር ጥሪና የተቃዋሚዎች ምላሽ

ሰኞ፣ ነሐሴ 10 2002

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህገመንግስቱንና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህገመንግስቱንና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ከሚቀበል ማንኛውም ድርጅትም ሆነ ግለሰብ ጋር ለመደራደር ዝግጁ እንደሆኑ ገለጹ። ተቃዋሚዎች ጥሪው የተለመደ የፖለቲካ ጨዋታ ሲሉ አጣጥለውታል።

https://p.dw.com/p/OorH
ጠ/ሚር መለስ ለተቃዋሚዎች የድርድር ጥሪ አቅርበዋልምስል AP Photo

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ጥሪውን ያቀረቡት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጪያ ነው። ህገመንግስቱ ለድርድር እንደማይቀርብ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚያ በመለስ ከየትኛው አካል ጋር ለመደራደር መንግስታቸው ዝግጁ ነው ብለዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት የሰጡት ኦነግና ግንቦት 7 የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ ጊዜ ያለፈበት የፖለቲካ

ቁማር ብለውታል። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የምክር ቤት አባልና ቃል አቀባይ ዶክተር በያን አሦባ እንደሚሉት ለድርድር ምንም ቅድመ ሁኔታ አያስፈልግም። የግንቦት 7 የፍትህ የዲሞክራሲና ንቅናቄ ሊቀመንበር ዶክተር ብርሀኑ ነጋ በበኩላቸው ድርጅታቸው ጥሪውን ከቁምነገር የሚቆጥረው አይደለም። ገዢው ፓርቲ ቀውስ ሲገጥመው የሚቀርበው የተለመደ ጨዋታ ብለዋል-ዶክተር ብርሀኑ። የፓለቲካና የህግ ምሁር ዶክተር ለማ ይፍራሸዋ ጥሪው አዲስ ባይሆንም የሰላም እስከሆነ ድረስ የሚደገፍ ነው ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል።

መሳይ መኮንን

ነጋሽ መሐመድ