1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያና የሱዳን ወታደራዊ ኃይል ማቋቋም ስምምነት

ሰኞ፣ ነሐሴ 12 2006

ኢትዮጵያ እና ሱዳን የጋራ ወታደራዊ ኃይል ለመመሥረት መስማማታቸዉን በይፋ ተናግረዋል። የመገናኛ ዘዴዎች እንደዘገቡት፤ ሁለቱ ሃገራት ለማቋቋም የወሰኑት የመከላከያ ኃይል አንድ እዝ ስር የሚታዘዝ ነዉ። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ፤ መሰጡት መግለጫ ጥምሩ ጦር እስከ መጭዉ መስከረም ወር ማብቂያ ድረስ እንደሚቋቋም ገልፀዋል።

https://p.dw.com/p/1CwX7
Infografik Flüchtlinge in Afrika

የሱዳን መከላከያ ሚኒስትር አብዱል ራሂም ሞሃመድ ሁሴን፤ በበኩላቸዉ የጋራ ጦር ኃይል መቋቋሙ፤ ቀደም ሲል በሁለቱ አገሮች መካከል የነበረዉን የሰላምና የፀጥታ ትብብር የበለጠ ያጠናክረዋል ሲሉ ተናግረዋል።

AU-Gipfel in Addis Abeba, Äthiopien, 31.01.2014 Omar al-Bashir
ምስል Reuters

ኢትዮጵያ እና ሱዳን በአንድ እዝ ሥር የሚንቀሳቀስ ጥምር የመከላከያ ኃይል ለመቋቋም ስምምነት ላይ መድረሳቸዉን ያሳወቁት ባለፈዉ ሳምንት ማክሰኞ፤ አዲስ አበባ ላይ 11ኛዉን የመከላከያ ሚኒስትሮች ስብሰባ ካጠናቀቁ በኋላ ባሳለፉት ዉሳኔ እንደሆነ ተመልክቶአል። የሁለቱ ሃገራት ጥምር የመከላከያ ኃይል ከፊታችን መስከረም ወር ጀምሮ እንደሚቋቋም መረጃ መዉጣቱን የሚገልፁት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ጉዳይ መምህር አቶ ደመቀ አጭሶ፤ ስምምነቱ ለአካባቢዉ ሃገራት ፋይዳ አለዉ ሲሉ ገልፀዋል።
ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን የድንበር ላይ ግጭትን ለማቆም በየግዜዉ ሥምምነት ላይ ቢደርሱም ገቢራዊነቱ አሁንም አጠያያቂ እየሆነ ነዉ። የኢትዮጵያ እና የሱዳን የጋራ የመከላከያ ኃይል መቋቋም በደቡብ ሱዳን እንዴት ይገመገም ይሆን መምህር ደመቀ፤ እንደሚሉት የሁለቱ ሃገሪት መቀራረብ ምናልባትም በአፍሪቃዉ ቀንድ ላሉት ሃገራት መቀራረብ ምሳሌ ይሆናል። እንዲያም ሆኖ በደቡብ ሱዳን ላይ የሚያመጣዉ ጫና አይኖርም፤ በሃገራቱ ድንበር አካባቢ የሚታየዉን የፀጥታ ጉዳይ ከማስጠበቅ በቀር።
ኢትዮጵያ አባይ ላይ እየገነባች ያለዉን ግድም ተከትሎ ኢትዮጵያ እና ግብፅ በአባይ ዉኃ አጠቃቀም ከሁነኛ ስምምነት ላይ አልደረሰም። ጉዳይ በቃላት እየተጣዘጠዙ ይገኛሉ። የሱዳን እና የኢትዮጵያ የጋራ የመከላከያ ኃይል መቋቋም ግብፅን ስጋት ላይ አይጥል ይሆን፤በተለይ በዉኃ ፖለቲካ ላይ ትኩረታቸዉን ያደረጉት አቶ ደመቀ አጭሶ፤ ግብፅ፤ ከዚህ በፊት የያዘችዉን የዉኃ መርህ ሊያስቀይራትና ወደ ትብብሩ ጎራ እንድትቀላቀል ያደርጋታል ሲሉ ተናግረዋል።

Nil Dammbau in Äthiopien Archiv 28.05.2013
ምስል William Lloyd-George/AFP/Getty Images

ሙሉዉን ቃለ ምልልስ የድምፅ ማእቀፉን በመጫን ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ