1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያና የኤርትራ የሠላም ተስፋ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 12 2005

ኤርትራ ለአፍሪቃ ህብረትና ለምስራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ኢጋድ አምባሳደር መላክዋ በቅርቡም ኢትዮጵያ የኤርትራ ወዳጅ ከሆነችው ከቀተር ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መጀመሯ ና ኢትዮጵያም ከኤርትራ ጋር ለመደራደር ዝግጁነቷን ማሳወቋ የፖለቲካ ተንታኞች በበጎ ምልክትነት ወስደውታል ።

https://p.dw.com/p/177m7


ኢትዮጵያና ኤርትራ የአልጀርሱ የሰላም ስምምነት ከተፈረሙ ወዲህ ሰላምም ጦርነትም በሌለበት ሁኔታ ውስጥ ነው ያሉት ። ሁለቱን ሃገራት ጦር ያማዘዘው ባድመ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አደራዳሪነት ፍርድ ከተሰጠበት በኋላም መግባባት ላይ አልተደረሰም ። ባለፉት አመታትም የአሜሪካን የቅርብ ወዳጅ ኢትዮጵያ የአካባቢው ሰላም ጠባቂ ፤ ኤርትራ ደግሞ የአካባቢው አዋኪ ተብለው ተፈርጀዋል ። የመንግሥታቱ ድርጅት ለአፍሪቃ ቀንድ አለመረጋጋት ተጠያቂ ባደረጋት በኤርትራ ላይ ማዕቀብ ጥሏል ። ኤርትራ ለሚጣልባት ማዕቀብም ሆነ ለሚደርስባት ወቀሳ ኢትዮጵያን ተጠያቂ ታደርጋለች ። በነዚህና በሌሎችም ምክንያቶች የኢትዮጵያና የኤርትራ ግንኙነት መሻሻል ሳይታይበት ዘልቋል ። ይሁንና በመካከሉ ኤርትራ ለአፍሪቃ ህብረትና ለምስራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ኢጋድ አምባሳደር መላክዋ በቅርቡም ኢትዮጵያ የኤርትራ ወዳጅ ከሆነችው ከቀተር ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መጀመሯ ና ኢትዮጵያም ከኤርትራ ጋር ለመደራደር ዝግጁነቷን ማሳወቋ የፖለቲካ ተንታኞች በበጎ ምልክትነት ወስደውታል ። ለመሆኑ በኤርትራ ና በኢትዮጵያ መካከል ሠላም የመውረዱ ተስፋ እስከምንድረስ ነው ? የውይይታችን ትኩረት ነው

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ