1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያና የኬንያ የፀጥታ ኃይሎች የድንበር ላይ ግጭት

ማክሰኞ፣ ኅዳር 14 2008

የኢትዮጵያ ወታደሮች ድንበር አቋርጠው ከኬንያ የጸጥታ ሃይሎች ጋር መጋጨታቸውና ሶስት የኬንያ ፖሊሶች መገደላቸውን ጋዜጦች ዘግበዋል። ግጭቱን ተከትሎ ኬንያ ወታደሮቿን ወደ ድንበር አስጠግታለች።

https://p.dw.com/p/1HC0F
Karte Ethiopia und Eritrea ENG

[No title]

ይህ ሲፈጠር የመጀመሪያ አይደለም። በተለያዩ ጊዜያት በኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር አካባቢ ተመሳሳይ ግጭቶች ተከስተዋል። በአሁኑ ግጭት የሶስት ህግ አስከባሪዎች ህይወት መጥፋት ግን ጉዳዩን የተለየ አድርጎታል። በአሁኑ ግጭት ላይ የኢትዮጵያም ሆነ የኬንያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ያሉት ነገር የለም። ኬንያ ዋና የሚገኘው የዶይቼ ቬለ ዘጋቢ ፋሲል ግርማ ጥቃቱ የተፈጸመበት አካባቢ ባለስልጣናት በጉዳዩ ላይ ከኢትዮጵያ መንግስት ግልጽ ማብራሪያ እንደሚፈልጉ ማስታወቃቸውን በስልክ ነግሮናል።

ፋሲል ግርማ

እሸቴ በቀለ

አርያም ተክሌ