1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያና የደቡብ ሱዳን ስምምነት

ዓርብ፣ የካቲት 17 2009

በፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር የተመራዉ የደቡብ ሱዳን ከፍተኛ የመልዕክተኞች ጓድ  ከኢትዮጵያ አቻዎቹ ጋር የተፈራረመመዉ ሥምምነት የንግድ፤የመንግድ ሥራ፤ የኤሌክትሪክ ኃይል ሺያጭና የጋዜጠኝነት ሥልጠናን የሚያካትት ነዉ

https://p.dw.com/p/2YDZo
Äthiopien Addis Abeba Salva Kiir Mayardit und  Hailemariam Desalegn
ምስል DW/Y. G/Egzibahre

(Beri.AA) Kirr besuch in AA - MP3-Stereo

የኢትዮጵያ መንግስት፤ በርስ በርስ ጦርነትና በረሐብ ከተመሰቃቀለችዉ ከደቡብ ሱዳን መንግሥት ጋር የተለያዩ ምጣኔ ሐብታዊ እና ሙያዊ ሥምምነቶችን ተፈራረመ።አዲስ አበባን የጎበኘዉ በፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር የተመራዉ የደቡብ ሱዳን ከፍተኛ የመልዕክተኞች ጓድ  ከኢትዮጵያ አቻዎቹ ጋር የተፈራረመመዉ ሥምምነት የንግድ፤የመንግድ ሥራ፤ የኤሌክትሪክ ኃይል ሺያጭና የጋዜጠኝነት ሥልጠናን የሚያካትት ነዉ።ደቡብ ሱዳን እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር ከ2013 ጀምሮ በርስበርስ ጦርነት እየወደመች ነዉ።አሁን ደግሞ በመቶ ሺሕ የሚቆጠር ሕዝቧ ለገዳይ ረሐብ ተጋልጧል።ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር በአዲስ አበባ ያደረጉትን ጉብኝት ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ተከታትሎታል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ